ንፁህ የመጠጥ ውሃ ተደራሽ ለማድረግ የተለያዩ ፕሮጀክት ወደ ተግባር ገብተዋል-ከንቲባ አዳነች አቤቤ

You are currently viewing ንፁህ የመጠጥ ውሃ ተደራሽ ለማድረግ የተለያዩ ፕሮጀክት ወደ ተግባር ገብተዋል-ከንቲባ አዳነች አቤቤ

AMN ጥር 30/2018 ዓ.ም

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አዳነች አቤቤ በቀን 37 ሺህ 996 ሜ.ኩብ ውሃ መስጠት የሚያስችሉ የ21 ጥልቅ ጉድጓዶች ቁፋሮ ሥራ ሙሉ በሙሉ መጠናቀቁን ተናገሩ።

ከዚህ ውስጥ በቀን 3 ሺህ 996 ሜ.ኩብ ውሃ መስጠት የሚያስችሉ 3 ጉድጓዶች ወደ ስርጭት ሲስተም እንዲገቡ መደረጉን ከንቲባ አዳነች አቤቤ የውኃ ልማት ዘርፍ አስመልክተው ባቀረቡት የአፈጻጸም ሪፖርት ለምክር ቤት አባላት ገልጸዋል፡፡

በተጨማሪም በቀን 100 ሺህ ሜ.ኩብ ውኃ ማምረት ከሚያስችል የጭቋላ ዌል ፊልድ የውሃ ልማት ፕሮጀክት ጋር ተያይዞ ከ24 ጉድጓዶች ውስጥ የ20 ጉድጓዶች ቁፋሮ ሥራ በታቀደው መሠረት ሙሉ በሙሉ መጠናቀቁን ከንቲባ አዳነች አቤቤ ተናግረዋል።

እነዚህን ጉድጓዶችን ወደ ስርጭት ሲስተም ለማስገባት እየተሰራ መሆኑንም ጠቁመዋል፡፡

በሌላ በኩል በቀን 20ሺህ ሜ.ኩብ ፍሳሽ የማጣራት አቅም ያለው የኮዬ ፈጬ የፍሳሽ ማጣሪያ ጣቢያ ግንባታ 75 በመቶ መጠናቀቁ አስታውቀዋል።

ከንቲባዋ ባቀረቡት ሪፖርት በፍሳሽ ልማት ዘርፍ የከተማዋን ህብረተሰብ ክፍል የዘመናዊ ፍሳሽ አገልግሎት ተደራሽነት ለማሳደግ የሚያስችሉ 8 ፕሮጀክቶች ተቀርጸው በመሰራት ላይ እንደሚገኙ ተናግረዋል።

በተመሳሳይ በቀን 106ሺህ ሜ.ኩብ ፍሳሽ የማጣራት አቅም የሚኖረው የምሰራቅ ተፋሰስ ፍሳሽ ማጣሪያ ጣቢያ ግንባታ ፕሮጀክትም በታቀደው መሠረት 30% መድረሱ ጠቁመዋል፡፡

እንዲሁም 20 ነጥብ 02 ሚሊዮን ሜትር ኪዩብ ከመኖርያ ቤቶች የሚፈጠረውን ፍሳሽ ቆሻሻ በመስመር እና በተሸከርካሪ በማሰባሰብ ለማጣራት እና ለማስወገድ ታቅዶ 19 ነጥብ 73 ሚሊዮን ሜትር ኪዩብ ፍሳሽ ቆሻሻ በማጣራት የእቅዱን 99 በመቶ ማሳካት መቻሉን ለምክር ቤት አባላት ገልጸዋል፡፡

በትዝታ መንግስቱ

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review