AMN-የካቲት 02/2018 ዓ.ም
ባንኩ ከዛሬ ጀምሮ “ለላቀ የደንበኞች እርካታ እንተጋለን” በሚል መሪ ሐሳብ ለአንድ ሳምንት የሚቆይ የደንበኞች ሳምንት መርሀግብር አስጀምሯል።
በመላ ሀገሪቱ በሚገኙ 1 ሺህ ቅርንጫፎቹ 24 ሰዓት አገልግሎት በሚሰጡ የዲጂታል ባንኪንግ አገልግሎት ደንበኞቹ እያገለገለ መሆኑን በዚህም ከአንድ ትሪሊየን ብር በላይ የዲጂታል ክፍያ ስርዓት ማከናወኑን የባንኩ ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ ፀሐይ ሽፈራው ተናግረዋል።

ባንኩ ከደንበኞች ጋር ያለውን ግንኙነት ይበልጥ ለማጠናከር እየሰራ መሆኑን አንስተው፤ ስራ ፈጣሪዎችና አምራቾች ሀሳባቸውን ወደ ቢዝነስ እንዲቀይሩ በማስቻል ረገድም ተጨባጭ ለውጥ ማስመዝገቡን አንስተዋል።
የደንበኞች ሳምንት መርሐ ግብሩ ደንበኞችን ለማመስገን እና እውቅና ለመስጠት፣ የባንኩን ሰራተኞች ለተሻለ ስራ ለማነሳሳት እንዲሁም የደንበኞችን አስተያየት በመቀበል ለበለጠ ለውጥ ለመስራት ያለመ ነው ተብሏል።
ደንበኞች በአቅራቢያቸው የአገልግሎት መስጫ ማዕከላት ቀልጣፋ አገልግሎት ለመስጠት ቅርንጫፎችን እያስፋፋ እና የዲጂታል ባንኪንግ ስርዓትን በበለጠ ለማዘመን እየሰራ እንደሚገኝም ተገልጿል።
በአይናለም አባይነህ