አዲስ አበባ ለአፍሪካ አንድነት ድርጅት መቀመጫነት ለምን ተመረጠች?

You are currently viewing አዲስ አበባ ለአፍሪካ አንድነት ድርጅት መቀመጫነት ለምን ተመረጠች?
  • Post category:አፍሪካ

• ቅኝ ያልተገዛች ብቸኛ ጥቁር አፍሪካዊት ሀገር በመሆኗ ለአፍሪካውያን “የነጻነት ቀንዲል” ሆና መታየቷ፣

• ኢትዮጵያ በአፍሪካ ቀንድ የምትገኝና ለሰሜን፣ ለደቡብ፣ ለምሥራቅና ለምዕራብ አፍሪካ ሀገራት አማካይ ርቀት ላይ በመገኘቷ ለጉዞና ለግንኙነት ምቹ ሆና በመገኘቷ፥

• የኢትዮጵያ አየር መንገድ አፍሪካን ከአውሮፓና ከእስያ ጋር የሚያገናኝ ቀዳሚ አየር መንገድ በመሆኑ ዲፕሎማቶችና መሪዎች በቀላሉ ወደ አዲስ አበባ እንዲመላለሱ ትልቅ ዕድል መፍጠሩ፥

• በአጼ ኃይለ ሥላሴ ዲፕሎማሲያዊ ጥረት በሁለቱ ተፋላሚ ጎራዎች (ሞንሮቪያ እና ካዛብላንካ ግሩፕ) መካከል የነበረው ልዩነት በማስታረቃቸው አዲስ አበባ በሁሉም ዘንድ ተቀባይነት ማግኘቷ፣

• ድርጅቱ ሳይመሠረት አዲስ አበባ ዘመናዊ የስብሰባ አዳራሽ (Africa Hall) እና ዓለም አቀፍ ደረጃቸውን የጠበቁ ሆቴሎችን ገንብታ መጠበቋ፣ መሪዎቹ ሌላ አማራጭ እንዳያማትሩ ማድረጉ፣

• አዲስ አበባ ከቀን ወደቀን በማያቋርጥ ዕድገት ውስጥ የምትገኝ በመሆኗ በየጊዜው የፈጠረችው ተቀባይነት የኢትዮጵያ ብቻ ሳይሆን የአፍሪካም መዲና እንድትሆን አድርጓታል።

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review