AMN- የካቲት 4/2018 ዓ.ም
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ከሳዑዲ አረቢያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ልዑል ፋይሰል ቢን ፋርሃን አል ሳዑድን በሁለትዮሽ እና ባለብዙ ወገን ጉዳዮች ላይ ውይይት አድርገዋል፡
ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማህበራዊ ትስስር ገፃቸው ባስተላለፉት መልዕክት ዛሬ የሳዑዲ አረቢያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ልዑል ፋይሰል ቢን ፋርሃን አል ሳዑድን ተቀብዬ በሁለትዮሽ እና ባለብዙ ወገን ጉዳዮች ላይ ውጤታማ ውይይት አድርገናል ብለዋል።
ጠቅላይ ሚኒስትሩ አክለውም ውይይታችን በዐበይት ዘርፎች ለረዥም ዘመናት የዘለቀውን የሁለቱ ሀገሮቻችንን ትስስር በማስፋት እና የወል ፍላጎቶቻችን በሆኑ ቀጣናዊ እና አለምአቀፋዊ ጉዳዮች ላይ ትብብራችንን በማጠናከር ላይ ያተኮረ ነበር ብለዋል፡፡