AMN የካቲት 4/2018 ዓ.ም
የአፍሪካ ሀገራት የንግድና ኢንቨስትመንት በማሳደግ አስተማማኝ የኢኮኖሚ ምኅዳር ለመገንባት በአባል ሀገራት መካከል ትብብርን ማጠናከር እንደሚገባ የተባበሩት መንግሥታት የአፍሪካ ኢኮኖሚክ ኮሚሽን ገለጸ፡፡
በ48ኛው የአፍሪካ ሕብረት የሥራ አስፈፃሚ ምክር ቤት መደበኛ ስብሰባ ላይ ንግግር ያደረጉት የተባበሩት መንግሥታት የአፍሪካ ኢኮኖሚክ ኮሚሽን ዋና ፀኃፊ ክላቨር ጋቴቴ እንደተናገሩት የአፍሪካን የተፈጥሮ ሃብት የዕሴት ሰንለት በማሻሻል የአህጉሪቱን የኢኮኖሚ ዕድገት ማፋጠን ያስፈልጋል፡፡
’’ዘላቂ የውሃ ኑረትና ንጽህና ስርዓት፤ ለአጀንዳ 2063 ስኬት” በሚል መሪ ሃሳብ እየተካሄደ ባለዉ በዚህ ጉባኤ የአፍሪካን ዕምቅ የመሬት፣ የታዳሽ ኃይል፣ የማዕድንና የተፈጥሮ ሃብት ጸጋዎች እሴት ሰንሰለት በማሻሻል የአህጉሪቱን የኢኮኖሚ ዕድገት ማሳለጥ እንደሚያስፈልግ ኮሚሽነሩ አስገንዝበዋል።
የአፍሪካን የንግድና ኢንቨስትመንት አቅም ማሳደግ፣ በአባል ሀገራት መካከል በጠንካራ ትስስር መፍጠር እንዲሁም አስተማማኝ የኢኮኖሚ ምኅዳር መገንባት እንደሚያስፈልግ አጽንኦት ሰጥተዉ ተናግረዋል፡፡ የአፍሪካ አህጉራዊ ነፃ ንግድ ቀጣና ስምምነት ሙሉ ትግበራን ማፋጠን እንደሚገባም አንስተዋል።
ይታያል አጥናፉ