AMN – የካቲት 5፣ 2018 ዓ.ም።
የአፍሪካ-ጣሊያን ፎረም በአዲስ አበባ መካሔዱ ኢትዮጵያ አፍሪካን ከተቀረው ዓለም ጋር ለማስተሳሰር ያላትን አቅም የሚያሳይ መሆኑን የመንግስት ኮሚዩኒኬሽን አገልግሎት ገለጸ።
የአፍሪካ-ጣሊያን ፎረም መካሔድ ከጀመረበት ጊዜ አንስቶ ከሮም ውጪ ሲካሄድ የዘንድሮው ለመጀመሪያ ጊዜ ነው፡፡
የመንግሥት ኮሚዩኒኬሽን አገልግሎት በሳምንቱ የሚካሔዱትን የአፍሪካ-ጣሊያን እና የአፍሪካ ሕብረት ጉባዔን አስመልክቶ በዛሬው ዕለት ጋዜጣዊ መግለጫ ሰጥቷል።
የአፍሪካ ጣሊያን ፎረም፣ የአፍሪካና ጣሊያን ግንኙነት በአሕጉራዊና ዓለም አቀፋዊ ትብብር ዘርፎች ይበልጥ እንዲጠናከር የሚያደርግ ነው መሆኑን ገልጿል፡፡
በታደሠ ሽፈራው