ኢትዮጵያ በውሃ ዘላቂነትና ተደራሽነት ረገድ ግንባር ቀደም ሚና እየተጫወተች ነው

You are currently viewing ኢትዮጵያ በውሃ ዘላቂነትና ተደራሽነት ረገድ ግንባር ቀደም ሚና እየተጫወተች ነው

AMN-የካቲት 05/2018 ዓ.ም

ኢትዮጵያ በትክክለኛ አመራርና ፖሊሲዎች በመመራት በውሃ ዘላቂነትና ተደራሽነት ረገድ ግንባር ቀደም ሚና እየተጫወተች መሆኑን የአፍሪካ ህብረት የኢኮኖሚ፣ ማህበራዊና ባህላዊ ምክር ቤት ሴክሬታሪያት ኃላፊ ዊሊያም ካሪው ገለጹ።

የአፍሪካ ህብረት የኢኮኖሚ፣ ማህበራዊና ባህላዊ ምክር ቤት ሴክሬተሪያት ኃላፊ ዊሊያም ካሪው የኢትዮጵያ መንግስት እያሳየ ያለው የአመራር ሚና ለመላው የአፍሪካ ህብረት እጅግ መሰረታዊ መሆኑን ጠቁመዋል።

የአፍሪካ ህብረት አባል ሀገራት በማናቸውም አባላት ዘንድ የተዘረጉ መልካም ተሞክሮዎችንና ፖሊሲዎችን በአርአያነት መጠቀም እንዳለባቸው ተናግረዋል።

የኢትዮጵያ መንግስት እያሳየ ያለው የአመራር ሚና ለመላው የአፍሪካ ህብረት እጅግ መሰረታዊ መሆኑን የጠቆሙት ኃላፊው እንደ የአፍሪካ ህብረት አባልነታችን በማናቸውም አባል ሀገሮቻችን ዘንድ ተግባራዊ የተደረጉ መልካም ተሞክሮዎችን እና ፖሊሲዎችን እንዴት እንደ መነሻ መጠቀም እንደምንችል ማየት ያስፈልጋልም ብለዋል።

በዚህ ረገድ የኢትዮጵያ መንግስት ለዘላቂ የውሃ አቅርቦትና ተደራሽነት አስተዋጽኦ የሚያደርጉ ፖሊሲዎችንና አሰራሮችን መዘርጋቱን መጠቆማቸውን ኢዜአ ዘግቧል።

ይህም ለሌሎች የአፍሪካ ህብረት አባል ሀገራት መልካም ተሞክሮ መሆኑን ጠቁመዋል።

በተወሰዱ የፖሊሲ ለውጦችና ቆራጥ የአመራረ ሰጭነት ኢትዮጵያ ባለፉት ዓመታትከ48 ቢሊዮን በላይ ችግኞችን በመትከል ያስመዘገብችውን ስኬት አድንቀዋል። ይህ ትልቅ ቁጥር መሆኑን ገልጸው ሁሉም የአመራርና ትክክለኛ ፖሊሲዎች ውጤት መሆኑን ጠቁመዋል።

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review