AMN- የካቲት 7/2018 ዓ.ም
ውሃ ለህዝቦች ጤና፣ ለኢኮኖሚ እድገት፣ ለቀጣናዊ መረጋጋት እና የሰላም እና የትብብር መሠረት እንጂ የግጭት ምንጭ ሊሆን አይገባውም ሲሉ የአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን ኮሚሽነር መሐመድ አሊ ዩሱፍ ገልጸዋል፡፡
39ኛው የአፍሪካ ኅብረት የመሪዎች ጉባዔ የአፍሪካ መዲና በሆነችው አዲስ አበባ በመካሄድ ላይ ይገኛል፡፡
በጉባኤው የአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን ኮሚሽነር መሐመድ አሊ ዩሱፍ፣ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)፣ የተባበሩት መንግስታት ዋና ፀሐፊ አንቶኒዮ ጉተሬዝ እና የጣሊያን ጠቅላይ ሚኒስትር ጆርጂያ ሜሎኒን ጨምሮ የህብረቱ ዓባል ሀገራት መሪዎችና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል፡፡
በመርሐ-ግብሩ የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የአፍሪካ ህብረት ኮሚሽነር መሐመድ አሊ ዩሱፍ፣ 35ኛው የአፍሪካ ህብረት የመሪዎች ጉባኤ በአህጉሪቱ የተለያዩ የፖለቲካ ቀውሶች፣ የውጭ ጣልቃ ገብነት እና ዓለም አቀፋዊ የኢኮኖሚ መከፋፈል በከፍተኛ ደረጃ እያሳሰበ በሚገኝበት ወቅት እየተካሄደ መሆኑን ጠቅሰዋል፡፡
ጉባኤው “ውሃ እና ንጽህና” በሚል መሪ ሀሳብ በጋራ ሀብት አጠቃቀም ላይ ቢመክርም፣ የአህጉሪቱ ህልውና እና የጂኦፖለቲካዊ ቀውሶች የውይይቱ ዋነኛ አጀንዳ እንደሚሆኑ ገልጸዋል።
በታምራት ቢሻው