AMN – የካቲት 7 ፣ 2018
ኢትዮጵያ በሰላማዊ አማራጮች ሁሉ አስተማማኝ የባህር በር ተደራሽነትን ማረጋገጥ መሠረታዊ ጉዳይ መሆኑን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ገለጹ፡፡
39ኛው የአፍሪካ ኅብረት የመሪዎች ጉባዔ “ዘላቂ የውኃ አቅርቦትና ደኅንነቱ የተጠበቀ የንጽህና አጠባበቅ ሥርዓቶችን ማረጋገጥ፤ ለአጀንዳ 2063 ግቦች ስኬታማነት” በሚል መሪ ሐሳብ በአዲስ አበባ እየተካሄደ ነው፡፡
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ባደረጉት ንግግር ኢትዮጵያ የምትመኘውን ዕድገት እውን ለማድረግ ሁሉንም የመገናኛ አውታሮችን የማስፋትና የማሳደግ ሥራዎችን እያከናዎነች መሆኗን ዘርዝረዋል፡፡
በየአየር ማረፊያ ግንባታ ፣ በቴሌኮም፣ በመንገድ ልማት እየሰራቻቸው ያሉ ግዙፍ ፕሮጀክቶችን ጠቅሰዋል፡፡
እንደ ኢትዮጵያ ላሉ ከፍተኛ የህዝበ ቁጥር ላላት ሀገር ከዓለም የምትገናኝበት አማራጮች ሊሰፉ እንደሚገባ አጽንኦት ሰጥተዋል፡፡
አስተማማኝ የባህበር ተደራሽነቷን ማረጋገጥ ለህልውናዋ ወሰኝ መሆኑን ነው ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) የገለጹት፡፡
በታደሰ ሽፈራው