“ምዝበራ ይቁም፤ የአፍሪካ ሀብት ለአፍሪካ ሕዝብ ይሁን”- አንቶኒዮ ጉቴሬዝ

You are currently viewing “ምዝበራ ይቁም፤ የአፍሪካ ሀብት ለአፍሪካ ሕዝብ ይሁን”- አንቶኒዮ ጉቴሬዝ

AMN- የካቲት 7/2018 ዓ.ም

39ኛው የአፍሪካ ኅብረት የመሪዎች ጉባዔ የአፍሪካ መዲና በሆነችው አዲስ አበባ በመካሄድ ላይ ይገኛል፡፡

በጉባኤው ንግግር ያደረጉት የተባበሩት መንግስታት ዋና ፀሃፊ አንቶኒዮ ጉተሬዝ አፍሪካ በዓለም አቀፍ መድረክ የሚገባትን ውክልና እና ፍትሃዊ ተጠቃሚነት ልታገኝ ይገባል ሲሉ ተናግረዋል ።

ዋና ጸሐፊው አህጉሪቱ በፀጥታው ምክር ቤት ቋሚ መቀመጫ ሊኖራት እንደሚገባ ነው ያሰሰቡት ።

ዋና ጸሐፊው በሱዳን፣ በዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ፣ በሶማሊያ እና በሌሎች የአህጉሪቱ ክፍሎች ያሉ ግጭቶች በአስቸኳይ እንዲቆሙም ጥሪ አቅርበዋል።

በተለይም የአፍሪካ የሰላም ድጋፍ ተግባራት አስተማማኝ ፋይናንስ እንዲያገኙ የተጀመሩ ጥረቶች ተጠናክረው እንደሚቀጥሉም አረጋግጠዋል።

አፍሪካ ለዓለም የአየር ንብረት መዛባት የምታበረክተው አስተዋጽኦ አነስተኛ ቢሆንም፣ የችግሩ ቀዳሚ ተጠቂ መሆኗን ጉቴሬዝ አስታውሰዋል።

ስለሆነም አህጉሪቱ ካላት የፀሐይ ኃይል አቅም ውስጥ የምታገኘው ኢንቨስትመንት 2 በመቶ ብቻ መሆኑ አግባብ እንዳልሆነ ጠቅሰው፣ “ምዝበራ ይቁም፤ የአፍሪካ ሀብት ለአፍሪካ ሕዝብ ይሁን” ሲሉ በአጽንኦት ገልጸዋል።

ዋና ጸሐፊው አያይዘውም የሥራ ዘመናቸው እስከሚያበቃበት ጊዜ ድረስ ከአፍሪካ ጎን እንደሚቆሙም አረጋግጠዋል።

በታምራት ቢሻው

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review