አርሰናል ወደ ሞሌንዩ አቅንቶ ዎልቭስን ይገጥማል

You are currently viewing አርሰናል ወደ ሞሌንዩ አቅንቶ ዎልቭስን ይገጥማል

AMN የካቲት 11 ቀን 2018 ዓ.ም

በእንግሊዝ ፕሪምየር ሊግ አርሰናል ወደ ሞሌንዩ ስታዲየም በማቅናት ዎልቭስን የሚገጥምበት ጨዋታ ይጠበቃል፡፡ ጨዋታው አርሰናል የካራባኦ ካፕ ፍፃሜ ተፋላሚ በመሆኑ ቀደም ብሎ እንዲከናወን መርሃ ግብር የወጣለት ነው፡፡

አርሰናል ጨዋታውን ካሸነፈ ከተከታዩ ማንችሰተር ሲቲ ያለውን የነጥብ ልዩነት ወደ ሰባት ለማስፋት ጥሩ አጋጣሚ አግኝቷል፡፡ የሰሜን ለንደኑ ክለብ ከብሬንትፎርድ ጋር 1ለ1 መለያየቱ ያሰጋቸው የክለቡ ደጋፊዎች በዛሬው ጨዋታ ከቡድናቸው ሦስት ነጥብ ይጠብቃሉ፡፡

መቼ የሚለው ካልሆነ በቀር መውረዱ የማይቀረው ዎልቭስ ትግሉ ከታሪክ ጋር ነው፡፡

የሮብ ኤድዋርድሱ ቡድን ከ26 ጨዋታ መሰብሰብ የቻለው ዘጠኝ ነጥብ ብቻ ሲሆን በዚሁ ካጠናቀቀ የፕሪምየር ሊጉ መጥፎው ክለብ ይሰኛል፡፡ ከዚህ ቀደም ደርቢ ካውንቲ በ2007/08 የውድድር ዓመት 11 ነጥብ ብቻ ሰብስቦ ነበር ያጠናቀቀው፡፡

አርሰናል ዎልቭስ ላይ ያለው ክብረወሰን የሚያኩራረ ነው፡፡ መድፈኞቹ ከዎልቭስ ጋር ያከናወኑትን የመጨረሻ ዘጠኝ የሊግ ጨዋታዎች በሙሉ አሸንፈዋል፡፡

ዛሬ ምሽት 5 ሰዓት በሚከናወነው ጨዋታ ላይም ይህን የበላይነታቸውን ካስቀጠሉ ነጥባቸውን 60 በማድረስ ተከታያቸው ላይ ጫና መፍጠር ይችላሉ፡፡

በጨዋታው በአርሰናል በኩል ሚካኤል ሜሪኖ እና ካይ ሃቨርትዝ በጉዳት አይሳተፉም ፤ ቤን ዋይት እና ሪካርዶ ካላፊዮሪ ግን ለጨዋታው ዝግጁ ናቸው።

በሸዋንግዛው ግርማ

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review