AMN- የካቲት 11/2018 ዓ.ም
የአርጆ የደንጋይ ክሰል ፋብሪካ፤ ኢትዮጵያ የአካባቢ ጥበቃን በማረጋገጥ የኢንደስትሪ ልማትን እንደምታሳድግ ማሳያ ነው ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ገለጹ፡፡
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)በማህበራዊ ትስስር ገፃቸው ባሰፈሩት መልዕክት፣ የአርጆ የደንጋይ ክሰል ፋብሪካ፤ ከውጭ ሲገባ የነበረውን የተፈጨ ድንጋይ ፍላጎት በሀገር ውስጥ በማሟላት በኢትዮጵያ የዘርፉ የኢንደስትሪ ልማት ዐቢይ ሚና ይጫወታል ብለዋል።

ፋብሪካው ለሲሚንቶ፣ ለብረት እና ኮንስትራክሽን ኢንደስትሪዎች አስፈላጊ ጥሬ ግብዓቶችን ያቀርባል። በተጨማሪም ፕሮጀክቱ ኢትዮጵያ የአካባቢ ጥበቃን በማረጋገጥ የኢንደስትሪ ልማትን እንደምታሳድግ ማሳያ ነው ሲሉም አክለዋል፡፡