ምክር ቤቱ የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽንን የስራ ዘመን ለ8 ወራት አራዘመ

You are currently viewing ምክር ቤቱ የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽንን የስራ ዘመን ለ8 ወራት አራዘመ

የካቲት 11/2018

የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽንን የስራ ዘመን ለ8 ወራት እንዲራዘም የቀረበውን የውሳኔ ሀሳብ በሙሉ ድምፅ አጸደቀ።

ምክር ቤቱ ዛሬ ባካሄደው የ5ኛ ዓመት የስራ ዘመን 1ኛ አስቸኳይ ስብሰባ የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን የእስካሁን የስራ አፈጻጸም ሪፖርት ላይ በመወያየት ቀጣይ አቅጣጫዎችን አስቀምጧል።

የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን ዋና ኮሚሽነር ፕሮፌሰር መስፍን አርዓያ ባለፉት አራት ዓመታት በሀገር ውስጥና በውጭ የተካሄዱ የአጀንዳ ማሰባሰብና የተሳታፊ ልየታ ተግባራትን በዝርዝር አቅርበዋል።

በምክር ቤቱ የዴሞክራሲ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ እውነቴ አለነ፥ ኮሚሽኑ ባለፉት ዓመታት ለቀጣይ የምክክር ሂደቱ ተግባራት ወሳኝ መሰረት የሚጥሉ ሥራዎችን ማከናወኑን ጠቅሰዋል።

በቀጣይም ቀሪ ሥራዎችን እንዲያጠናቅቅ ተጨማሪ የስምንት ወራት ጊዜ እንዲሰጠው ለምክር ቤቱ የውሳኔ ሀሳብ አቅርበዋል።

ምክር ቤቱም የቀረበውን የውሳኔ ሀሳብ በሙሉ ድምጽ አጽድቋል።

በፍቃዱ መለሰ

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review