በግብርና የጀመርነው እመርታ በአግሮ ኢንዱስትሪ ፋብሪካዎች ካልተደገፈ ውጤታማ አይሆንም- ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ

You are currently viewing በግብርና የጀመርነው እመርታ በአግሮ ኢንዱስትሪ ፋብሪካዎች ካልተደገፈ ውጤታማ አይሆንም- ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ

AMN- የካቲት 12/2018 ዓ.ም

በግብርና የጀመርነው እመርታ በአግሮ ኢንዱስትሪ ፋብሪካዎች ካልተደገፈ ውጤታማ አይሆንም ሲሉ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ ገልጸዋል፡፡

ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማህበራዊ ትስስር ገፃቸው ባሰፈሩት መልዕክት፣ ዛሬ ከጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ.ር) ጋር የነቀምቴ የተቀናጀ የግብርና ኢንዱስትሪ ፓርክን ጎብኝተናል ብለዋል።

ይህ የተቀናጀ የግብርና ኢንዱስትሪ ፓርክ በኦሮሚያ ኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን፣ በ250 ሄክታር መሬት ላይ እየተገነባ የሚገኝ ነው።

ፓርኩ በአካባቢው ለሚገኙ፣ በተለይም በአራቱ የወለጋ ዞኖች ለሚገኙ ገበሬዎች ታላቅ የገበያ ዕድል የፈጠረ ነው ያሉት።

የገበሬዎችን ምርት ይረከባል፤ ያቀነባብራል፤ እንዲሁም ለሀገር ውስጥና ለውጭ ገበያ ያቀርባል ያሉት ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ፣ በግብርና የጀመርነው እመርታ በአግሮ ኢንዱስትሪ ፋብሪካዎች ካልተደገፈ ውጤታማ አይሆንም ብለዋል።

በዚህ ረገድ በኦሮሚያ ክልል የተጀመረው ተግባር የግብርና ዕድገታችንን የሚያሣልጥ ነው በማልት ገልጸዋል።

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review