AMN- የካቲት 12/2018 ዓ.ም
ዛሬ ያስጀመርነው የቡሳ ጎኖፋ ኦሮሚያ የተቀናጀ የምግብ ኢንዱስትሪ ግንባታ የበቆሎ እና አኩሪ አተር ዱቄት እንዲሁም 14 ተጓዳኝ የበቆሎ ውጤት ምርቶችን ለማምረት የታቀደ ነው ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ገለጹ፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማህበራዊ ትስስር ገፃቸው ባሰፈሩት መልዕክት፣ ፕሮጀክቱ ተጠናቆ ወደ ስራ ሲግባ በቀን 2 ሺህ ቶን በቆሎ እና 120 ቶን ማሽላ የማምረት አቅም ይኖረዋል ብለዋል።
ከ6 ሺህ 500 በላይ ለሚሆኑ ሠራተኞች ቋሚ እና ጊዜያዊ የሥራ እድል የሚፈጥር ሲሆን፣ ለአካባቢው አርሶአደሮች፣ ለኅብረት ሥራ ማኅበራት እና የግል ዘርፍ አምራቾች የእሴት ሰንሰለትን በማገዝ ለአካባቢው አርሶአደሮች ሰፊ ገበያ ይፈጥራል፣ የአካባቢውን ኢኮኖሚ ያሳድጋል ብለዋል።