– በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ተግባራዊ እየተደረገ የሚገኘው የ”ኢትዮጵያ ታምርት” አካል የሆነው “አዲስ አበባ ታምርት” ንቅናቄ በከተማዋ ኢኮኖሚ ላይ አዲስ ተስፋና ተጨባጭ ለውጥ እያስመዘገበ ይገኛል።
– ንቅናቄው የከተማዋን የኢኮኖሚ መዋቅር በመቀየር ረገድ የላቀ ሚና እየተጫወተ ነው።
– ከዚህ በፊት በግብዓትና በኤሌክትሪክ እጥረት ከአቅም በታች ያመርቱ የነበሩ ፋብሪካዎች፣ አሁን ላይ የማምረት አቅማቸውን በከፍተኛ ሁኔታ አሳድገዋል።
– በአዲስ አበባ ጎዳናዎች ላይ “የኢትዮጵያን ምርት ይግዙ” የሚለው ጥሪ ዛሬ በተጨባጭ ውጤት ታጅቦ በምግብና መጠጥ፣ በጨርቃጨርቅና በኮንስትራክሽን ዘርፎች ከውጭ የሚገቡ ምርቶችን በሀገር ውስጥ ጥራት ባላቸው ምርቶች መተካት ተችሏል።
– ንቅናቄው በሺዎች ለሚቆጠሩ ወጣቶችና ሴቶች ቋሚና ጊዜያዊ የሥራ ዕድል ከመፍጠሩም ባለፈ፣ የቴክኖሎጂና የክሕሎት ሽግግር እንዲመጣ አድርጓል።

– በርካታ አነስተኛ አምራቾች ወደ መካከለኛ ኢንዱስትሪነት ተሸጋግረዋል፤ ጠንካራ የገበያ ትስስርም ተፈጥሮላቸዋል።
– ከጫማ እስከ አልባሳት፣ ከቤት ዕቃዎች እስከታሸጉ ምግቦች ድረስ አዲስ አበባ ከውጭ የምታስገባቸውን ምርቶች በሀገር ውስጥ መተካት አስችሏታል።
– የከተማ አስተዳደሩ ለዘርፉ ስኬት ቁልፍ የሆኑ ድጋፎችን እያከናወነ ይገኛል።
– በከተማዋ በተለያዩ ክፍለ ከተሞች የተገነቡ ሼዶች ለወጣቶችና ለባለሀብቶች ተላልፈው፣ አዲስ አበባን የኢንዱስትሪ ማዕከል እያደረጓት ይገኛሉ።
– ዘመናዊ የኢንዱስትሪ መንደሮችን በማስፋፋት ለአምራቾች ምቹ የሥራ ቦታ እንዲሆኑ ማድረግ ተችሏል።
– ለኢንተርፕራይዞች የማሽነሪ ግዢ የሚውል የሊዝ ፋይናንስና የብድር አገልግሎት እንዲመቻችና የቢሮክራሲ ማነቆዎችን የሚፈታ “የአንድ ማዕከል” አገልግሎት እንዲቋቋም ተደርጓል።
– የባንክ በሮች ለአምራቾች ክፍት ሆነዋል። ንቅናቄው አምራቾች በቀላሉ የሥራ ማስኬጃ ብድር የሚያገኙበትን መንገድ ከማመቻቸቱም በላይ፣ በቀጥታ ከሸማቹ ጋር የሚገናኙባቸውን ታላላቅ ባዛሮች በማዘጋጀት የገበያ ሰንሰለቱን አሳጥሮታል።
– በተጨማሪም አምራቾች ምርቶቻቸውን እንዲያስተዋውቁ ትላልቅ ባዛሮችንና ኤግዚቢሽኖችን በማዘጋጀት በኩልም ከፍተኛ አስተዋጽዖ እያደረገ ይገኛል።
በአስማረ መኮንን