የፖለቲካ ፖርቲዎች የመወዳደሪያ ምልክት የማስተዋወቂያና የእጩዎች የስነ ምግባር ደንብ መፈረሚያ መርሀ ግብር ተካሄደ

You are currently viewing የፖለቲካ ፖርቲዎች የመወዳደሪያ ምልክት የማስተዋወቂያና የእጩዎች የስነ ምግባር ደንብ መፈረሚያ መርሀ ግብር ተካሄደ
  • Post category:ፖለቲካ

AMN የካቲት 14/2018 ዓ.ም

በ7ተኛው ጠቅላላ ምርጫ ለመወዳደር የተመዘገቡ የፖለቲካ ፖርቲዎች የመወዳደሪያ ምልክት የማስተዋወቂያና የእጩዎች የስነ ምግባር ደንብ መፈረሚያ መርሀ ግብር ተካሄዷል፡፡

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ከተሠጡት ሕገ መንግስታዊ ስልጣንና ሀላፊነቶች መካከል ምርጫን በነፃነትና በገለልተኝነት ማስፈፀም አንዱ ነው፡፡

ቦርዱ ለ7ተኛው ጠቅላላ ምርጫ የተመዘገቡ 48 የፖለቲካ ፓርቲዎችን የመወዳደሪያ ምልክት የማስተዋወቂያ መርሀ ግብር አካሂዷል፡፡

የብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ዋና ሰብሳቢ ወ/ሮ ሜላትወርቅ ሀይሉ፣ ምርጫው ፍትሐዊ፣ነፃና ገለልተኛ እንዲሆን እየተሰራ መሆኑን ገልፀዋል።

መራጩ ህዝብ የሚመርጠውን የፖለቲካ ፓርቲ ለይቶ ማወቅ እንዳለበት ታሳቢ ያደረገ መርሐ ግብር መሆኑንም ጠቁመዋል።

ሀገራዊ ምርጫን በሰለጠነ መንገድ ማካሔድ እንደሚያስፈልግ የገለፁት ዋና ሰብሳቢዋ፣ ይህንን ለማሳካትም ተወዳዳሪ የፓለቲካ ፓርቲዎች የሚገዙበት የስነ ምግባር ደንብ መዘጋጀቱን ተናግረዋል።

ለሂደቱ ሠላማዊነትና ዴሞክራሢያዊነት የሁሉም ተሣትፎ ወሳኝ ስለመሆኑም አመላክተዋል።

በመርሀ ግብሩ የፓለቲካ ፓርቲ አመራሮችና የሲቪክ ማህበረሠብ ድርጅቶች እየቸሣተፉ ነው።

በጸጋ ታደለ

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review