ራስ አሉላ አባ ነጋ!!

You are currently viewing ራስ አሉላ አባ ነጋ!!

ኢትዮጵያውያን አርበኞች በዱር በገደሉ ደማቸውን አፍሰው፣ አጥንታቸውን ከስክሰው በከፈሉት የሕይወት ዋጋ ለእኛ ልጆች ሀገርን ከነክብሯ አስረክበውናል።

ኤ.ኤም.ኤንም ከእነዚህ ሕያው ምስክሮች መካከል የዓድዋ ጀግኖችን እየዘከረ ይገኛል፡፡

በዓድዋ ጦርነት ከመላ ኢትዮጵያ የመጡ አርበኞችና ሀገር ወዳድ ዜጎች በ12 የጦር አዝማቾች መሪነት ታላቅ ድል አስመዝግበዋል፡፡ ከጦር መሪዎቹ መካከል ራስ አሉላ አባ ነጋ አንዱ ናቸው፡፡

የጦሩ ጀግና ራስ አሉላ አባ ነጋ፣ ጣሊያንን ደጋግመው ደቁሰዋል፡፡ በጥር 1879 የኢጣልያ ጦርን ምጽዋ ላይ በመግጠም፣ 500 የሚጠጉ የጣሊያን ወታደሮችን ድል በማድረግ የመጀመሪያውን ትልቅ ድል ተቀዳጅተዋል።

ቀጥሎም በዓድዋ ጦርነት ዋዜማ በሺዎች የሚቆጠር ጦር ያሰለፈው ጄነራል ባራቶሪ አምባላጌንና መቀሌን ሊቆጣጠር የጦር ስልት በነደፈ ጊዜ በታላቅ ወታደራዊ ጥበብ መክተዋል፡፡

በታሪካዊው የዓድዋ ጦርነት ወቅት ደግሞ የግራ ክንፍ ጦርን በመምራት በጄነራል አልቤርቶኒ የሚመራውን ሠራዊት በሶሎዳ ተራራ በመደምሰስና በመማረክ ታላቅ ታሪክ ሰርተዋል።

በሁሉም ጦርነቶች ጀብዱ የፈጸሙት የኢትዮጵያ የቁርጥ ቀን ልጅ ራስ አሉላ የሀገር ባለውለታነታቸው በጦር ሜዳ ብቻ አልነበረም፡፡ በዲፕሎማሲ፣ በፍትሕ፣ እንዲሁም ዳር ድንበር የሚጠብቀው ሠራዊት ደመወዝ እንዲከፈለው ያደረጉ ታላቅ ሰው ነበሩ፡፡

አሉላ አባ ነጋ በዓድዋ ድል ማግስት የካቲት 9 ቀን 1889 በክብር ማረፋቸው በታሪክ ተመዝግቧል፡፡

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review