የልዩ ዘመቻዎች እዝ ባለፉት 65 ዓመታት በበርካታ ፈተናዎች ውስጥ የማይበገር ጽናት ይዞ ኢትዮጵያን ያኮራ ጀብዱ ፈጽሟል – ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር)

You are currently viewing የልዩ ዘመቻዎች እዝ ባለፉት 65 ዓመታት በበርካታ ፈተናዎች ውስጥ የማይበገር ጽናት ይዞ ኢትዮጵያን ያኮራ ጀብዱ ፈጽሟል – ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር)

AMN – የካቲት 14 ፣ 2018ዓ.ም

የመከላከያ ሠራዊት የልዩ ዘመቻዎች እዝም ባለፉት 65 ዓመታት በበርካታ ፈተናዎች ውስጥ የማይበገር ጽናት ይዞ ኢትዮጵያን ያኮራ ጀብዱ መፈጸሙን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) ገለጹ፡፡

‎የእዙን 65ኛ ዓመት የምስረታ በዓሉን አስመልክቶ በማሕራዊ ትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት መልዕክት ፣ እዙ አሁን ላይ በመከላከያ ሪፎርም ስራዎች አማካኝነት አየር ወለድ፣ ኮማንዶ እና ልዩ የጸረ ሽብር ኃይል በመያዝ በአደረጃጀት፣በሠው ኃይል እና በትጥቅ ዘመኑን በዋጀ መልኩ ተዋቅሮ በየትኛውም ጊዜና በማንኛውም ሁኔታ ግዳጁን በብቃት ለመፈጸም በአስተማማኝ ቁመና ላይ ይገኛል ብለዋል፡፡

ኢትዮጵያ በትውልድ ቅብብሎሽ ሀገር ያጸኑ የበርካታ ጀግኖች ምድር ናት ሲሉም ነው ጠቅላይ ሚኒስትሩ የገለጹት፡፡

‎እዙ 65ኛ ዓመት የምስረታ በዓሉን ሲያከብር የገነባውን የዘመነ ወታደራዊ አቅም፣ የሰው ኃይል ዝግጁነት እና የታክቲክ ብቃት ለሕዝብ ይፋ ማድረጉን በመልዕክታቸው ጠቅሰዋል፡፡

በተለይም ዛሬ የቀረበው የተቀናጀ የውሃ ላይ ልምምድ ፣ የአየር ወለድና የኮማንዶ አባላት በቅንጅት ያሳዩት ልዩ ልዩ ወታደራዊ ክህሎት የሠራዊቱን ከፍተኛ ብቃት ያረጋገጠ መሆኑን ጠቅላይ ሚኒስተር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) ገልጸዋል፡፡

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review