AMN- የካቲት 15/2018 ዓ.ም
ኢትዮጵያ የትናንት ታሪክን አክብራ እና ዘክራ ወቅቱ የሚዋጀውን የልማት አውድን እውን አድርጋ ሁለንተናዊ ምሉዕነትን ለመላበስ እየሰራች መሆኑን የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አዳነች አቤቤ ተናግረዋል፡፡
ትናንት በደም እና በአጥንታቸው የሀገርን ዳር ድንበር ያስከበሩ ህዝባቸውንም በክብር ያኖሩ አባቶች መታሰቢያ በሆነው በአድዋ ድል መታሰቢያ አድዋን የሚዘክር የማስ ስፖርት ተደርጓል፡፡
የአድዋ ድል ትሩፋቱ ዘርፈ ብዙ የማሸነፋችን ሚስጥር አንድነት እና ህብረት ነው ያሉት ከንቲባ አዳነች የአሁኑ ትውልድ አንድነትን ከትናንት አባቶቹ ወርሶ ዘመኑ በሚጠይቀው አውድ እና የልማት ግስጋሴ ላይ አሻራዉን ያሳርፍ ዘንድ ጠይቀዋል፡፡
አሁን ላይ አድዋ በልማት እየተደገመ ነዉ ያሉት ከንቲባዋ ታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ እና በከተሞች እየተሰሩ ያሉ ልማቶች ለዚህ ማሳያ ናቸው ብለዋል፡፡
የአድዋ ድል ሚስጥር ህብረት እና አንድነት ነው ያሉት ከንቲባ አዳነች አቤቤ፣ የአሁኑ ትውልድም ህብረት እና አንድነቱን ያጠናክር ዘንድ ጠይቀዋል፡፡
በተመስገን ይመር