AMN – የካቲት 14/2018 ዓ.ም
ማንችስተር ሲቲ ኒውካስትል ዩናይትድን በማሸነፍ ከአርሰናል ያለውን የነጥብ ልዩነት ወደ ሁለት አጥብቧል።
በኢትሃድ ስታዲየም የተከናወነውን 27ኛ ሳምንት የሊጉ መርሐግብር ጨዋታ ሲቲ 2ለ1 አሸንፏል።
እንግሊዛዊው አማካይ ኒኮ ኦራይሊ ሁለቱንም የሲቲ ግቦች በመጀመሪያው አጋማሽ አስቆጥሯል።
ሊውስ ሃል የኒውካስትል ዩናይትድን ብቸኛ ግብ ማስቆጠር ችሏል።
ማንችስተር ሲቲ በሁለተኛው አጋማሽ በአብዛኛው ጨዋታ እንደተከሰተው ጥሩ ባይጫወትም ውጤቱን አስጠብቆ ወጥቷል።
ውጤቱን ተከትሎም ማንችስተር ሲቲ ነገ ከቶተንሃም ጋር ፈታኝ ጨዋታ ከሚጠብቀው አርሰናል ያለውን የነጥብ ልዩነት ሁለት ብቻ ማድረግ ችሏል።
በሸዋንግዛው ግርማ