ጁቬንቱስ ከአውሮፓ ቻምፒየንስ ሊግ ውድድር ውጪ ሆነ

You are currently viewing ጁቬንቱስ ከአውሮፓ ቻምፒየንስ ሊግ ውድድር ውጪ ሆነ

AMN- የካቲት 18/2018 ዓ.ም

ጁቬንቱስ በአውሮፓ ቻምፒየንስ ሊግ የጥሎ ማለፍ የመልስ ጨዋታ ጋላታሳራይን አስተናግዶ 3ለ2 ቢረታም በድምር ውጤት ተሸንፎ ከውድድሩ ውጪ ሆኗል።

በመጀመሪያው ጨዋታ 5ለ2 የተሸነፈው የጣልያኑ ክለብ ማኑኤል ሎካቴሊ በፍፁም ቅጣት ምት ፣ ፌድሪኮ ጋቲ እና ዌስተን ማኬኒ ባስቆጠሯቸው ግቦች ድምር ውጤቱን አቻ ማድረግ ችሎ ነበር።

በጭማሪ 30 ደቂቃ ላይ ቪክቶር ኦሲምኸን እና ባሪስ አልፐር ይልማዝ ለጋላታሳራይ ያስቆጠሯቸው ግቦች ግን የጁቬንቱስን ድካም መና አስቀርተዋል።

ጁቬ እስከ መጨረሻው የተፋለመው 48ኛው ደቂቃ ላይ ተከላካዩ ሎይድ ኬሊን በቀጥታ ቀይ ካርድ አጥቶ ነው።

በድምር ውጤት 7ለ5 ያሸነፈው ጋላታሳራይ በቀጣይ ዙር ከሊቨርፑል ወይም ከቶተንሃም አንዱን ይገጥማል።

በሸዋንግዛው ግርማ

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review