ከተፈረሙ የመግባቢያ ሰነዶች መካከል 32ኛውን የተባበሩት መንግሥታት የአየር ንብረት ጉባዔ (COP32) ማዘጋጀት፣ በግብርና፣ በሚዲያ ልማትና ልምድ ልውውጥ፣ በኢንቨስትመንት ማስፋፊያ እና በጸረ-ሙስና ትብብር ዙሪያ የሚያጠነጥኑ ናቸው።
በሌላ በኩል የአዘርባጃንን የአገልግሎት ዘርፍ ዝመናን በግንባር ቀደምትነት እየመራ የሚገኘው ተቋም “አሳን” (ASAN) እና በኢትዮጵያ የመሶብ አገልግሎት መካከል በጋራ ለመስራት ስምምነት ላይ ተደርሷል።
እነዚህ ስምምነቶች እና የመግባቢያ ሰነዶች በሁለቱ ሀገራት መካከል ባሉ ቁልፍ ዘርፎች የሁለትዮሽ ትብብርን ይበልጥ እንደሚያጠናክሩ እና እንደሚያሰፋፉ ይጠበቃል። – የጠቅላይ ሚኒስትር ጽ/ቤት