የካቲት 21/2018 ዓ.ም
ላለፉት ስምንት ቀናት በአዲስ አበባ ደረጃ ሲካሄድ የቆየው የ2018 ዓ/ም የኢትዮጵያ ታምርት ኤክስፓ ማጠቃለያ መርሃ ግብር በአዲስ አለም አቀፍ ኮንቬንሽን ማዕከል እየተካሄደ ይገኛል።
ንቅናቄው “ኢትዮጵያ ታምርት፤ አዲስ አበባ ትበልፅግ” በሚል መሪ ቃል ነው ሲካሄድ የቆየው።
በማጠቃለያ መርሀ ግብሩ የተገኙት የአዲስ አበባ ከተማ ምክትል ከንቲባና የኢንዱስትሪ ልማት ቢሮ ኃላፊ አቶ ጃንጥራር አባይ፤ የከተማ አስተዳደሩ ለአምራቹ ዘርፍ የቅድሚያ ቅድሚያ ሰጥቶ እየሰራ ይገኛልብለዋል።

የኢትዮጵያ ታምርት ንቅናቄን በፋይናንስ፣ በሰው ሀይል፣ በመሰረተ ልማት፣ በገበያ ትስስርና በሌሎችም ዘርፎች በማገዝ ለዛሬ ውጤት መብቃት ተችሏል ሲሉም ገልፀዋል።
የአምራቹ ዘርፉ የታለመለትን ግብ ይመታ ዘንድ የፓሊሲ ማሻሻያ በማድረግ እና አደረጃጀቶችን በመፍጠር በአምራቾች የሚነሱ ጥያቄዎችን የመመለሱ ተግባር ተጠናክሮ ይቀጥላል ብለዋል።
በዘርፉ ያለውን ችግር የመፍታቱ ተግባር ለመንግስት ብቻ የሚተው አለመሆኑን ያነሱት አቶ ጃንጥራር፤ የግሉ ዘርፍም በትኩረት በመስራት ማደግ ይጠበቅበታል ሲሉ ገልፀዋል።
በማጠቃለያ መርሀ ግብሩ የተሻለ አፈፃፀም ላላቸው አምራቾችና አጋር አካላት እውቅናና ሽልማት የተበረከተ ሲሆን፤ በፕሮግራሙ የአዲስ አበባ ከተማ ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች ተገኝተዋል።
በአዲስ አበባ 3ሺህ 900 አነስተኛ እና ትላልቅ ኢንዱስትሪዎች የሚገኙ ሲሆን እነዚህ አምራቾች ተኪ ምርቶችን በማምረት የውጭ ምንዛሬን በማስቀረት የሀገርን እድገት እያፋጠኑ ስለመሆኑ በማጠቃለያ መርሀ ግብሩ ተጠቅሷል።
በንጉሱ በቃሉ