የተመለከትነው የኢትዮጵያን ታሪክና ለውጥ ብቻ ሳይሆን የአፍሪካን ጭምር ነው -ጎብኝዎች

You are currently viewing የተመለከትነው የኢትዮጵያን ታሪክና ለውጥ ብቻ ሳይሆን የአፍሪካን ጭምር ነው -ጎብኝዎች

AMN የካቲት 21/ 2018 ዓ.ም

የተለያዩ የአፍሪካ ሀገራት መከላከያ ሚኒስትሮች፣ ወታደራዊ አታሼዎች፣ አምባሳደሮች፣ የአፍሪካ ህብረትና የተባበሩት መንግሥታት ተጋባዦችና እንግዶች የተለያዩ የልማት ተቋማትን እየጎበኙ ነዉ፡፡

ጎብኘዎቹ የእንጦጦ ፓርክን ፣ ሳይንስ ሙዚየም እንዲሁም የአድዋ ድል መታሰቢያ ሙዚየምን ተዘዋውረው የተመለከቱ ሲሆን በአጭር ጊዜ የተሰሩ ጠቅላላ የልማት ሥራዎችን በተመለከተ ሰፊ ገለፃ ተደርጎላቸዋል።

ኢትዮጵያም አዲስ አበባም በጣም ተቀይረዋል በአየነው ነገር እጅግ ተደንቀናል። ከተሰራና ጥረት ከተደረገ ተጨባጭ ለውጥ ማምጣት እንደሚቻል ተገንዝበናል ሲሉ ጎብኘዎቹ ሀሳባቸውን አጋርተዋል።

የተመለከትነው የኢትዮጵያን ታሪክና ለውጥ ብቻ ሳይሆን የአፍሪካን ጭምር ነው ይህም ትውልዱ ቀደምት ታሪኩን አውቆ አዲሲቷን አፍሪካ እንድንሰራ እድል ይፈጥራል ብለን እናምናለንም ብለዋል።

ትልልቅ ሀገራዊ ፕሮጀክቶች በለውጡ መንግስት መሪነት እየተተገበሩ ሲሆን ኢትዮጵያ የአፍሪካ ተምሳሌትነቷ ከፍ እንዲል እና ለዜጎቿ ምቹ እንድትሆን ተደርጓል ማለታቸዉን የሃገር መከላከያ ኦንላይን ሚዲያ ለኤኤምኤን የላከዉ መረጃ ያመላክታል፡፡

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review