AMN- የካቲት 22/2018 ዓ.ም
በዓለም አትሌቲከስ የፕላቲኒየም ደረጃ በተሰጠው 19ኛው የቶኪዮ ማራቶን አትሌት ታደሰ ታከለ አሸነፈ ።
አትሌት ታደሰ ውድድሩን ለማጠናቀቅ 2: 03.37 ወስዶበታል፡፡
አትሌቱ ያሳለፍነው ዓመት የቶኪዮ ማራቶንን ማሸነፉ የሚታወስ ሲሆን፣ዘንድሮም ለተከታታይ ጊዜ ማሸነፍ ችሏል።
በውድድሩ የተሳተፉት ኢትዮጵያውያን አትሌቶች አትሌት ሙክታር እድሪስ በ2:04.07 የግል ምርጥ ስዓቱን በማስመዝገብ በመግባት 5ኛ፣ለሁለተኛ ጊዜ ማራቶን ውድድሩን ያካሄደው
አትሌት ሰለሞን ባረጋ በ2:05.00 በመግባት የግል ምርጥ ስዓቱን በማስመዝገብ
7ኛ ደረጃ በመያዝ ውድድራቸውን አጠናቀዋል ።
በሴቶች ምድብ አትሌት ብርቱኳን ወልዴ ሁለተኛ ደረጃ ወጥታለች ።
አትሌት ብርቱኳን ውድድሩን ለማጠናቀቅ 2:16.36 በመግባት የግል ምርጥ ስዓቷን አስመዝግባለች ።
ኢትዮጵያውያን አትሌቶች አትሌት ሀዊ ፈይሳ በ2:17.39 በመግባት ሶስተኛ
፣አትሌት ሱቱሜ አሰፋ በ2:17.39 በመግባት አራተኛ
አትሌት መገርቱ አለሙ በ2:18.50 በመግባት አምስተኛ ደረጃ በመያዝ ውድድራቸውን አጠናቀዋል ።
አትሌት ሱቱሜ አሰፋ ያለፉት ሁለት ተከታታይ ዓመታት ቶኪዮ ማራቶን ማሸነፏ የሚታወስ ነው።
ኬንያዊቷ አትሌት ብሪጅ ኮስጊ ውድድሩ በ2:14.29 በመግባት አሸንፋለች ።