የድሬዳዋ ኢንተርናሽናል ስታዲየም በጊዜያዊነት ፍቃድ አገኘ

You are currently viewing የድሬዳዋ ኢንተርናሽናል ስታዲየም በጊዜያዊነት ፍቃድ አገኘ

AMN- የካቲት 22/2018 ዓ.ም

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን በሜዳው የሚያደርጋቸውን ጨዋታዎች በሀገሩ ለማድረግ ለካፍ ያቀረበው ጥያቄን ተከትሎ የካፍ የስታዲየም ገምጋሚ ልዑክ ባሳለፍነው ረቡዕ የካቲት 18 ወደ ድሬዳዋ ስታዲየም በማምራት የስታዲየሙን ብቁነት ገምግሟል።

ባለሞያዎቹ ከግምገማ በኋላ ኢትዮጵያ በቀጣይ ከሳኦቶሜ እና ፕሪንሲፔ ጋር የምታደርገውን ጨዋታ በድሬዳዋ ኢንተርናሽናል ስታዲየም እንድታደርግ ጊዜያዊ ፈቃድ ሰጥቷል።

ካፍ ዛሬ በላከው ደብዳቤ ሜዳው ለአንድ ጨዋታ ብቻ በዝግ ጨዋታ እንዲከናወንበት ጊዜያዊ ፈቃድ መስጠቱን የኢትዮጵያ እግርኳስ ፌዴሬሽን አስታውቋል።

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ለዓመታት የሜዳ ጨዋታውን በሌላ ሀገራት ስታዲየም ሲያከናውን ቆይቷል። ይህ ቡድኑን ከፍተኛ ጫና ውስጥ ከመክተቱም በላይ ከፍተኛ የውጪ ምንዛሬ ሲወጣ ነበር።

በቀጣይ የባህርዳር ኢንተርናሽናል ስታዲየም እንዲሁም የአደይ አበባ ስታዲየም ዝግጁ ይሆናሉ ተብሎ ይጠበቃል።

በሸዋንግዛው ግርማ

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review