የዓድዋ የድል መንፈስ የሚጠየፈው ቅጥረኝነትን ነው – ፕሬዝዳንት ታዬ አጽቀስላሴ

You are currently viewing የዓድዋ የድል መንፈስ የሚጠየፈው ቅጥረኝነትን ነው – ፕሬዝዳንት ታዬ አጽቀስላሴ

AMN- የካቲት 23 ቀን 2018 ዓ.ም

130ኛው የዓድዋ ድል በዓል በዓድዋ ድል መታሰቢያ በድምቀት ተከብሯል።

በበዓሉ መልእክት ያስተላለፉት ፕሬዝዳንት ታዬ አጽቀሥላሴ የዛሬው የአድዋ ትርጉም ነጻነትን በብልጽግና ማስዋብ እና ለቀጣይ ትውልድ የሚተርፍ አኩሪ ተግባርን መፈጸም መሆኑን ተናገሩ።

ፕሬዝዳንቱ በመልዕክታቸው፣ በዓለም የተበተኑ ጥቁር ወንድሞቻችንና እህቶቻችን የነጻነት ቁጭትና የእኩልነት መሻታቸውን አባቶቻችን በጦር ሜዳ ጀግንነት እንደመለሱት ሁሉ፣ የዘመኑ ጀግኖችም ይህንን ጥሪ በስራ፣ በእውቀት እና ሀገርን በማሳደግና በማበልጸግ መመለስ እንደሚገባቸው አጽንኦት ሰጥተዋል።

የአድዋ መንፈስ የሚጠየፈው ቅጥረኝነትን ነው ያሉት ፕሬዝዳንት ታዬ፣ ከበርካታ የዓድዋ ዋና ተምሳሌቶች መካከል፣ ለውጭ ሃይላት ጋሻ ጃግሬነትን ከመለማመድ ይልቅ ለሀገር እና ለብሄራዊ ክብር ታማኝ መሆን አንዱ መሆኑን ይገባል ሲሉ መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል።

በፍሬሕይወት ብርሃኑ

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review