የባርሰሎና የ4ለ0 ውጤትን የመቀልባስ ፈተና

You are currently viewing የባርሰሎና የ4ለ0 ውጤትን የመቀልባስ ፈተና

AMN- የካቲት 24/2018 ዓ.ም

በኮፓ ዴል ሬይ የግማሽ ፍፃሜ የመልስ ጨዋታ ባርሰሎና አትሎቲኮ ማድሪድን በካምፕ ኑ ያስተናግዳል።

በዋንዳ ሜትሮፖሊታኖ የተደረገውን የመጀመሪያ ጨዋታ አትሌቲኮ ማድሪድ 4ለ0 ማሸነፉ ይታወሳል። በዚህ ጨዋታ በተለይ በዳኝነቱ ደስተኛ ያልነበሩት ባርሳዎች ውጤቱን የመቀልበስ ከባዱን ፈተና ለመወጣት ወደ ሜዳ ይገባሉ።

ከሮበርት ሌቫንዶቭስኪ ውጪ ከተሟላ ስብስቡ ጋር የሚገኘው ባርሰሎና ተጫዋቾቹ ታሪክ ለመስራት ዝግጁ እንደሆኑ አሰልጣኙ ሀንሲ ፍሊክ ተናግረዋል። የ61 ዓመቱ ጀርመናዊው አሰልጣኝ “ሁሉም የቡድን አባላት ውጤቱን ለመቀልበስ ጥሩ ተነሳሽነት ላይ ይገኛሉ።” ሲሉ ተናግረዋል። አትሌቲኮ ማድሪድ ይህን ውጤት በቀላሉ አሳልፎ ይሰጣል ተብሎ አይጠበቅም። በተለይ በመከላከሉ ረገድ ለባርሰሎና ፈታኝ ይሆናል ተብሎ ተገምቷል።

ተጠባቂው ጨዋታ ምሽት 5 ሰዓት ላይ ይጀምራል። ኮፓ ዴል ሬይን 32 ጊዜ ያሸነፈው ባርሰሎና የዛሬውን ጨዋታ በድምር ውጤት ካሸነፈ ለ44ኛ ጊዜ የፍፃሜ ተፋላሚ ይሆናል። የ10 ጊዜ የውድድሩ አሸናፊ አትሌቲኮ ማድሪድ በአንፃሩ 20ኛ ፍፃሜውን ለመድረስ ይፋለማል።

በሸዋንግዛው ግርማ

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review