ሪያል ማድሪድ በሄታፌ ተሸነፈ

You are currently viewing ሪያል ማድሪድ በሄታፌ ተሸነፈ

AMN- የካቲት 23/2018 ዓ.ም

በ26ኛ ሳምንት የስፔን ላሊጋ በሳንቲያጎ ቤርናቢዩ ሄታፌን ያስተናገደው ሪያል ማድሪድ 1ለ0 ተሸንፏል።

ማርቲን ሳትሪያኖ የሄታፌን የማሸነፊያ ኳስ ከመረብ አሳርፏል። ሄታፌ ከስምንት ተከታታይ ሽንፈት በኋላ ነው ሪያል ማድሪድን መርታት የቻለው።

በጨዋታው ጭማሪ ደቂቃ ላይ በማድሪድ በኩል ፍራንኮ ማስታንቱኖ በቀይ ካርድ ወጥቷል። የሄታፌው አድሪያን ሊሶም በሁለት ቢጫ በቀይ ካርድ ከሜዳ ወጥቷል። ዣቪ አሎንሶን አሰናብቶ አልቫሮ አርቤሎዋን በጊዜያዊነት የቀጠረው ማድሪድ ውጤቱ እንዳሰበው አልሆነለትም።

በኮፓ ዴል ሬይ በአልባሴቴ ተሸንፎ ከውድድር የወጣው ማድሪድ ከመሪው ባርሰሎና ያለውን የነጥብ ልዩነት ወደ አንድ የሚያጠብበትን እድል አልተጠቀመም። በአውሮፓ ቻምፒየንስ ሊግ ጥሎ ማለፍ ማንችስተር ሰቲን የሚገጥመው ቡድኑ ምናልባት አርቤሎዋንም ሊያሰናብት እንደሚችል ተገምቷል።

በሸዋንግዛው ግርማ

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review