ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) በትግሪኛ ቋንቋ ከኢዜአ ጋር በነበራቸው ቆይታ ካስተላለፏቸው መልዕክቶች

You are currently viewing ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) በትግሪኛ ቋንቋ ከኢዜአ ጋር በነበራቸው ቆይታ ካስተላለፏቸው መልዕክቶች

ለትግራይ ሕዝብና ወጣቶች ያስተላለፉት መልዕክት፡-

👉 “የትግራይ ሕዝብ ከጦርነት ይልቅ ሰላምና ልማት ይገባዋል” ብለዋል።

👉 ወጣቶች የስልጣን ባለቤት እንዲሆኑና በአሮጌ አስተሳሰብ ለጦርነት ከሚገፋፏቸው አካላት ራሳቸውን እንዲጠብቁ መክረዋል።

👉 መንግሥት በትግራይ ክልል ሰላም እንዲሰፍንና ዳግም ጦርነት እንዳይከሰት ጽኑ ፍላጎት እንዳለውና ለዚህም ማንኛውንም መስዋዕትነት እንደሚከፍል አረጋግጠዋል።

የሰሜኑን ጦርነት መንስኤዎች በተመለከተ

👉 ሕወሓት ከ50 ዓመት በፊት በነበረ ኋላቀር አስተሳሰብ የታሰረ መሆኑና ለውጥን ለመቀበል አለመፈለጉ። ዓለም በቴክኖሎጂና በ”ፕራግማቲዝም” በምትመራበት ዘመን፣ ድርጅቱ በአሮጌው መንገድ ለመጓዝ መሞከሩ ለግጭት ዳርጎታል።

👉 ቆሞ ቀሩ ኃይል “ኢትዮጵያ ትፈርሳለች” የሚል የተሳሳተ ስጋት በመዝራት የለውጡን ኃይል እንደ ጠላት ማየቱ።

የፕሪቶሪያው የሰላም ስምምነት ተግባራዊነት በተመለከተ ፡-

👉 መንግሥት የትግራይ ሕዝብ ሰላም እንዲያገኝ ባንክ፣ መብራትና ቴሌኮም የመሳሰሉ አገልግሎቶችን በፍጥነት እንዲመለሱ ማድረጉን ገልጸዋል።

👉 ሆኖም ቆሞ ቀሩ ቡድን ስምምነቱን “መርጦ የመተግበር” ዝንባሌ እያሳየ መሆኑን ተችተዋል። በተለይም ሕገ-መንግሥታዊ ሥርዓቱንና የብሔራዊ ምርጫ ቦርድን ውሳኔ አለማክበሩን ጠቅሰዋል።

👉 ድርጅቱ ለልማት የተመደበውን በጀት ለጦርነት ዝግጅትና ለታጣቂዎች ቀለብ እየዋለ መሆኑን ገልጸው፣ ይህም በትግራይ ሕዝብ ላይ ተጨማሪ መከራ እያመጣ መሆኑን አስገንዝበዋል።

በጦርነቱ ወቅት የተፈጸሙ የሰብዓዊ መብት ጥሰቶችን በተመለከተ፡-

👉 ጦርነት ሁልጊዜም አስከፊ ገጽታ እንዳለው ገልጸው፣ ተጠያቂነትን ለማረጋገጥ የሽግግር ፍትሕ (Transitional Justice) አስፈላጊ መሆኑን ጠቁመዋል።

👉 ይህ ሂደት ከፖለቲካ ወገንተኝነት ነፃ በሆነ መንገድ ሊካሄድ እንደሚገባውና ወንጀል የፈጸሙ አካላት በሕግ መጠየቅ እንዳለባቸው ገልጸዋል።

የኤርትራ መንግሥት (ሻዕቢያ) ሚና

👉 በጦርነቱ ወቅት የኤርትራ ጦር ያደረገው ድጋፍ የሚታወስ መሆኑን ጠቅሰዋል።

👉 ሆኖም በጦርነቱ ሂደት የተፈጸሙ ማናቸውም ዓይነት ጥፋቶች፣ ግድያዎችና ዘረፋዎች (በተለይም በአክሱም፣ ዓድዋና ሽሬ አካባቢዎች) የማይቀበሉትና የሚወገዝ ተግባር መሆኑን በግልጽ አስታውቀዋል።

👉 መንግሥት ማንኛውንም የውጭ ኃይል ጣልቃ ገብነት እንደሚቃወምና የሀገርን ሉዓላዊነት ለማስከበር እንደሚሠራ ገልጸዋል።

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review