AMN የካቲት 24/2018 ዓ.ም
ባለፉት አመታት የታየውን የሴቶች ተጠቃሚነት አጠናክሮ ማስቀጠል እንደሚገባ የአዲስ አበባ ሴቶች፣ ህፃናትና ማህበራዊ ጉዳይ ቢሮ ገለፀ፡፡
ቢሮው ዓለም አቀፍ የሴቶች ቀንን በማስመልከት ከተለያዩ ተፅዕኖ ፈጣሪ እና ለሌሎች አርአያ ከሚሆኑ ሴቶች ጋር የፓናል ውይይት እያካሄደ አካሂዷል፡፡
ይህ ቀን መከበሩ ሴቶች ዲሞክራሲያዊ መብታቸውን እንዲያስከብሩ እና ያላቸውን ተሳትፎ እንዲያሳድጉ ያስቻለ መሆኑንም የቢሮው ሀላፊ ወ/ሮ ቆንጅት ደበላ ተናግረዋል።
ባለፉት አመታት የታየው የሴቶች ተጠቃሚነት ሴቶችን ይበልጥ የሚያበረታታና ተሳታፊ የሚያደርግ መሆኑን ያነሱት ሀላፊዋ፣ ይህንንም አጠናክሮ ማስቀጠል እንደሚገባ አንስተዋል።
ሴቶችን ማብቃት ቤተሰብን፣ ማህበረሰብን እና ትውልድን ለመገንባት መሰረት መሆኑንም ወ/ሮ ቆንጅት አክለው ተናግረዋል።
ቢሮው በዓለም አቀፍ ለ115ኛ ጊዜ በኢትዮጵያ ደግሞ ለ50ኛ ጊዜ የሚከበረውን የዓለም የሴቶች ቀንን ”የ50 ዓመታት የሴቶች ድምፅ ለእኩልነት እና ለበለፀገች ኢትዮጵያ” በሚል መሪ ሀሳብ እያከበረ ይገኛል።
በአይናለም አባይነህ