AMN – የካቲት 25/2018 ዓ.ም.
የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ፬ኛ ፓትርያርክ የነበሩት የብጹዕ ወቅዱስ አቡነ መርቆሬዎስ በዓለ ዕረፍት 4ኛ ዓመት በመንበረ ጸባዖት ቅድስት ሥላሴ ካቴድራል በተለያዩ መንፈሳዊ መርሃ ግብሮች ታስቧል፡፡
በመታሰቢያ መርሐ ግብሩ ላይ ብጹዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳት፣ የአዲስ አበባ ገዳማትና አድባራት አስተዳዳሪዎች፣ የቤተክርስቲያኗ ሊቃውንት፣ የፓትርያርኩ ቤተሰቦችና እና ምዕመናን ተገኝተዋል።

ለ27 ዓመታት በስደት ከኖሩበት ሀገረ አሜሪካ ፓትርያርኩ የተመለሱት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በግል ጥረታቸው ለሁለት ተከፍሎ የነበረውን ሲኖዶስ እንዲዋሃድ ማድረጋቸውን ተከትሎ ነበር።
በሥነ-ሥርዓቱ ላይ ቅዱስነታቸው በፕትርክና ከተሾሙበት ጊዜ አንስቶ በሀገር ውስጥ እና ባሕር ማዶ በቆዩባቸው ዓመታት ለቤተክርስቲያን አንድነት የከፈሉት ዋጋ ተዘክሯል።
ቅዱስ ፓትርያርኩ ለ34 ዓመታት ቤተ ክርስቲያንን በመሪነት በማገልገል ከፍጹም ብሕትውና እና ሃይማኖታዊ ተጋድሎ ጋር ሲመተ ፕትርክናቸውን ባገኙበት ዕለት የካቲት 25 2014 ዓ.ም ዕረፍታቸው ሆኗል።
በወርቅነህ አቢዮ