በኢትዮጵያ በጉዳት ይወገዱ የነበሩ የሰውነት ክፍሎችን በዘመናዊ ቴክኖሎጂ በመታገዝ መመለስ ተችሏል

You are currently viewing በኢትዮጵያ በጉዳት ይወገዱ የነበሩ የሰውነት ክፍሎችን በዘመናዊ ቴክኖሎጂ በመታገዝ መመለስ ተችሏል
  • Post category:ጤና

AMN- የካቲት 25/2018 ዓ.ም

በኢትዮጵያ በተለያዩ አደጋዎች ጉዳት ደርሶባቸው ይወገዱ የነበሩ የሰውነት ክፍሎችን በዘመናዊ ቴክኖሎጂ በመታገዝ ወደ ነበረበት መመለስ መቻሉን የአለርት ኮምፕርሄንሲቭ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል ሥራ አስኪያጅ ዶክተር ሽመልስ ገዛኸኝ አስታውቀዋል፡፡

የአለርት ኮምፕርሄንሲቭ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል ካለፉት አሥር ዓመታት ወዲህ ተጨማሪ ህክምናዎችን አካቶ እየሰጠ ይገኛል፡፡

የአለርት ኮምፕርሄንሲቭ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል ሥራ አስኪያጅ ዶክተር ሽመልስ ገዛኸኝ ሆስፒታሉ በተፈጥሮና ሰው ሰራሽ አደጋዎች የሚከሰቱ የአካል ጉዳቶችን ጥንቃቄ በተሞላ የፕላስቲክ ሪኮንስትራክቲቭ ቀዶ ህክምና እንደሚሰጥ ለኤ ኤም ኤን ተናግረዋል።

ፕላስቲክ ሪኮንስትራክቲቭ ሰርጀሪ በተለያዩ ምክንያቶች ለአካል ጉዳት የሚያደርስን አደጋ በጥንቃቄ ረጅም ሰዓት ወስዶ ወደ ቦታው የመመለስ ስርዓት መሆኑን ያብራራሉ፡፡

አሁን ሙሉ በሙሉ በኢትዮጵያውያን ቀዶ ህክምና ባለሙያዎች ህክምናው እየተሰጠ በመሆኑ ታካሚዎች ወደ ውጭ ሀገር ሄደው ለህክምና የሚያወጡትን ወጪ እንደሚያስቀር ገልጸዋል፡፡

ለአብነትም አንድ ወጣት የብልት መቆረጥ በደረሰበት አደጋ ወደ አለርት ኮምፕርሄንሲቭ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል ህክምና ተቋም በማቅናት ጉዳት የደረሰበትን አካል መልሶ ለማዳን ለዘጠኝ ሰዓታት በዘመናዊ ቀዶ ህክምና ሂደት ሙሉ በሙሉ ተሳክቶ ታካሚው በጥሩ ሁኔታ ላይ እንደሚገኝ ዶክተር ሽመልስ ተናግረዋል።

በየተለያዩ ሀገራት ስልጠና ወስደው ብቁ በሆኑ ኢትዮጵያውያን ሀኪሞች እየተከናወነ የሚገኘው የፕላስቲክ ሪኮንስትራክቲቭ ቀዶ ህክምና አገልግሎት ኢትዮጵያ የደረሰችበትን የህክምና ደረጃ ማሳያ መሆኑም ተመላክቷል።

በትዝታ መንግስቱ

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review