AMN- የካቲት 25/2018 ዓ.ም
በ29ኛ ሳምንት የእንግሊዝ ፕሪምየር ሊግ አርሰናል ብራይተንን ሲያሸንፍ ፣ ማንችስተር ሲቲ ከኖቲንግሃም ፎረስት ጋር አቻ ተለያይቷል።
በአሜክስ ስታዲየም ብራይተንን እየገጠመው አርሰናል 300ኛ ጨዋታውን ባደረገው ቡካዮ ሳካ ግብ 1ለ0 አሸንፏል። በኢትሃድ ስታዲየም ኖቲንግሃም ፎረስትን ያስተናገደው ማንችስተር ሲቲ ጨዋታውን 2ለ2 አጠናቋል። ሲቲ በአንቷን ሴሜንዮ እና ሮድሪ ግቦች በሁለት አጋጣሚ የመምራት እድል ቢያገኝም ውጤቱን አላስጠበቀም።
የመውረድ ስጋት ያለበት ፎረስት በሞርጋን ጊብስ ዋይት እና ኤሊዮት አንደርሰን ግቦች ነጥብ ተጋርቷል። ውጤቱን ተከትሎ ማንችስተር ሲቲ አንድ ጨዋታ እየቀረው ከአርሰናል ያለው የነጥብ ልዩነት ወደ ሰባት ሰፍቷል።
በሌላ ጨዋታ ቼልሲ ወደ ቪላ ፓርክ አቅንቶ አስቶንቪላን 4ለ1 አሸንፏል። ጆአኦ ፔድሮ ሀትሪክ ሲሰራ ፣ ኮል ፓልመር ሌላኛውን ግብ አስቆጥሯል። ዳግላስ ሊውዝ የአስቶንቪላን ግብ ማስቆጠር የቻለ ተጫዋች ነው። ውጤቱን ተከትሎ ቼልሲ በ48 ነጥብ ወደ 5ኛ ደረጃ ከፍ ብሏል።
ወራጅ ቀጠና የሚገኘው ዌስትሃም ዩናይትድ ከሜዳው ውጪ ፉልሃምን 1ለ0 በመርታት ወሳኝ ድል አስመዝግቧል።ክሪሲዬንሶ ሰመርቪል የዌስትሃምን የድል ግብ አስቆጥሯል።
በሸዋንግዛው ግርማ