የካራማራ ጦርነት 48ኛ ዓመት የድል በዓል መታሰቢያ በአዲስ አበባ በመከበር ላይ ይገኛል

You are currently viewing የካራማራ ጦርነት 48ኛ ዓመት የድል በዓል መታሰቢያ በአዲስ አበባ በመከበር ላይ ይገኛል

AMN-የካቲት 26/2018

48ኛው የካራማራ ድል መታሰቢያ በዓል አዲስ አበባ ጥቁር አንበሳ ሆስፒታል አካባቢ በሚገኘው የኢትዮ-ኩባ የወዳጅነት ፓርክ በመከበር ላይ ይገኛል።

በአከባበር ስነ ስርዓቱ በጦርነቱ በመሳተፍ ብቻም ሳይሆን በፈጸሙት ጀብድ የሚጠቀሱ የቀድሞው ጦር ሰራዊት አባላት፣ የኢትዮ-ኩባ ወዳጅነት ማህበር አመራርና አባላት እንዲሁም በኢትዮጵያ የኩባ ወዳጆችና ሌሎችም እንግዶች ተገኝተዋል፡፡

በዓሉ ኢትዮጵያውያን በወራሪው የሶማሊያ የዚያድ ባሬ ጦር ያስመዘገቡትን ደማቅ ድል በማሰብ የሚከበር ነው፡፡

“ታላቋን ሶማሊያ” የመገንባት ውጥን ይዞ በ1970 ዓ.ም ምስራቃዊ ኢትዮጵያን የወረረው የዚያድ ባሬ ጦር በጀግና ኢትዮጵያውያን የተባበረ ክንድ ድባቅ ተመቶ ወደመጣበት መመለሱ ይታወቃል።

ከዛሬ 48 ዓመታት በፊት የካቲት 26 ቀን 1970 ዓ.ም የኢትዮጵያ ጦር ድንበር ጥሶ ወደ ኢትዮጵያ ሉዓላዊ ግዛት ገብቶ የነበረውን የሶማሊያን ሰራዊት ከኢትዮጵያ ግዛት በማስወጣት ካራማራ ተራራ ላይ የኢትዮጵያን ሰንደቅ ዓላማ ማወለብለቡን ታሪክ ያስታውሳል።

በሚካአል ህሩይ

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review