በመዲናዋ ህገ-ወጥ ግንባታና ማስታወቂያዎችን ለመግታት የተደረገው ቅንጅታዊ አሰራር ውጤት እያመጣ መሆኑ ተገለጸ

You are currently viewing በመዲናዋ ህገ-ወጥ ግንባታና ማስታወቂያዎችን ለመግታት የተደረገው ቅንጅታዊ አሰራር ውጤት እያመጣ መሆኑ ተገለጸ

AMN- የካቲት 26/2018 ዓ.ም

ሕገ-ወጥነትን ለመከላከል በቅንጅት በተሠሩ ሥራዎች፣ ሕገ-ወጥ ግንባታና ማስታወቂያዎችን መቀነስ መቻሉን የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የግንባታ ፈቃድና ቁጥጥር ባለሥልጣን እና የደንብ ማስከበር ባለሥልጣን ገለጹ።

ሁለቱ ተቋማት በ2018 በጀት ዓመት ባለፉት ሰባት ወራት ውስጥ በቅንጅት የተከናወኑ ሥራዎችን በጋራ ገምግመዋል።

በበጀት ዓመቱ ሰባት ወራት ሕገ-ወጥ የመሬት ወረራን፣ ሕገ-ወጥ ግንባታን እና ማስታወቂያዎችን ለመከላከል በተሠሩ ሥራዎች ስኬት መመዝገቡን የአዲስ አበባ ግንባታ ፈቃድና ቁጥጥር ባለሥልጣን ዋና ዳይሬክተር ኢንጅነር ሕይወት ሳሙኤል ገልጸዋል፡፡

ይህም አዲስ አበባን ዘመናዊ ከተማ የማድረግ ሂደት ውስጥ ትልቅ ሚና ነበረው ብለዋል።

የአዲስ አበባ ከተማ ደንብ ማስከበር ባለሥልጣን ዋና ሥራ አስኪያጅ ሻለቃ ዘርይሁን ተፈራ፣ በከተማዋ የሚካሄዱ ግንባታዎች ዘመናዊነታቸውን ጠብቀው እንዲከናወኑ በርካታ ሥራዎች በቅንጅት መሠራታቸውን የገለጹ ሲሆን፣ ተግባራቱ በበጀት ዓመቱ ቀሪ ወራትም ተጠናክረው እንደሚቀጥሉ አረጋግጠዋል።

በአለሙ ኢላላ

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review