2ሺህ መኪናዎች ማቆሚያ የተዘጋጀለት 5.5ኪ.ሜ. የመንገድ ኮሪደር

You are currently viewing 2ሺህ መኪናዎች ማቆሚያ የተዘጋጀለት 5.5ኪ.ሜ. የመንገድ ኮሪደር

AMN – 28/2018 ዓ.ም

በአዲስ አበባ የትራፊክ ፍሰት መጨናነቅ ከሚታይባቸው መስመሮች መካከል የኡራኤል እስከ ቦሌ ብራስ ያለው አንደኛው ነው፡፡

መስመሩ የመኪና መቆሚያ የሌለው ና መንገዱ መኪና ማቆሚያም፣ የመኪና ማሽከርከሪያም፣እግረኛም ተቀላቅሎ የሚቀሳቀስበት የነበረ መሆኑ ለትራፊክ ፍሰት መጨናነቁ ዋነኛ ምክንያት ሆኖ ቆይቷል፡፡

ከቦሌ ቪአይፒ ተርሚናል እስከ ኡራኤል ድረስ ባለው የ5.5ኪ.ሜ. የኮሪደር ልማት የተሰራው የመኪና ማቆሚያ ትልቅ ለውጥ የሚያመጣ ነው፡፡

የአዲስ አበባ ከንቲባ አዳነች አቤቤ ለኤ.ኤም.ኤን እንደተናገሩት 15 ቦታዎች ላይ የምድር መኪና ማቆሚያ የተዘጋጁ ሲሆን ፣ በየህንጻ ውስጥ ቀድሞም ተሰርተው አገልግሎታቸው ተቀይሮ ለፓርኪንግ እየዋሉ ያልነበሩ ወደ 100 አካባቢ ህንጻዎች የመኪና ማቆሚያ አገልግሎት እንዲሰጡ ተደርገዋል፡፡

እነዚህ 115 የመኪና ማቆሚያዎች ባጠቃላይ ወደ ሁለት ሺህ መኪናዎችን በአንድ ጊዜ የማቆም አቅምን በዚህ መስመር ላይ መፍጠራቸውን ከንቲባ አዳነች ገልጸዋል፡፡

እንደ ከንቲባዋ ገለጻ ፣ 1ሺ 100 መኪናቹ በህንጻዎች ውስጥ ማቆም የሚያስችል ሲሆን ፣ 9መቶ መኪናዎችን ውጪ ላይ የሚያቆም አቅም ነው፡፡

በየመኪና ማቆሚያዎቹ 56 የኤሌክትሪክ መኪና ቻርጂንጎች የገባለት ሲሆን ተጨማሪ ቻርጅ ማድረጊያዎች እንደሚገነቡም ነው የተገለጸው፡፡

ታክሲና አውቶቡስ መጠበቂያ ተርሚናሎች የተስተካከሉለት ሆኑ የተሳለጠ የትራፊክ ፍሰት እንዲኖረው የሚያስችል እንደሆነ ከንቲባ አዳነች አቤቤ ገልጸዋል፡፡

በታደሰ ሽፈራዉ

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review