AMN – 28/2018 ዓ.ም
ከቦሌ ቪአይፒ ተርሚናል እስከ ኡራኤል ድረስ ያለውን መንገድ የሚሸፍነው የኮሪደር ልማት ተጠናቆ ለአገልግሎት ክፍት ሆኗል፡፡
5.5 ኪሎ ሜትር ርዝመት ያለው ይህ መንገድ የአዲስ አበባን ውበት ከገለጡ ሥራዎች አንዱ ለመሆን በቅቷል፡፡
በኮሪድር ልማቱ የተከናወነው ከቀበና የሚመጣውን ወንዝ አትላስ አካባቢ ፣ ከፒኮክ ጋር እንዲገናኝ በማድረግ የተሰራው የማጽዳትና የማስዋብ የወንዝ ልማት ብክለትን በማስቀረት ፣ የሰዎችን ጤና እና ደህንነት በማስጠበቅ ትልቅ ለውጥ የተመዘገበበት ነው፡፡
ከንቲባ አዳነች አቤቤ በመዲናዋ የተከናወኑ የልማት ሥራዎችን አስመልክቶ በሰጡት ገለጻ ከዚያ የሚወጣው ብክለት ብዙዎችን ለበሽታ፣ ለሞት ይዳርግ እንደነበር ገልጸዋል፡፡
በጎርፍ ምክንያት በየመፋሰሻው በክረምት የሚመጣው ፍሳሽ እና ወንዙ ተቀላቅለው የብዙዎችን ህይወት ይቀጥፍ እንደነበር ነው ከንቲባ አዳነች አቤቤ ያስታወሱት፡፡
ይህን የአደጋ ታሪክ መቀየር የሚያስችል ልማት ነው በዚህ መስመር የተከናወነው።
ከንቲባ አዳነችም ልማቱ ”ያልተነገረ፣ ሚዲያም ሌላም አካል ያልተናገረው የከተማዋ ነዋሪ ላይ ይደርስ የነበረ ጉዳትን የተከላከለ ነው።” ብለዋል፡፡
አምስት ቦታዎች ላይ የህዝብ መፀዳጃ ቦታዎችን የተዘጋጀለት ይህ መስመር ፣ የበሽታና የሽታ ምንጭነቱ ተሰርዞ ብዙዎች ኑ የሚል የማረና የደመቀ ሆኗል፡፡
በታደሰ ሽፈራዉ