ዛሬ ወደተለያዩ 8 የዓለም ሀገራት በሴቶች ብቻ የሚመሩ በረራዎች በተመሳሳይ ሰዓት ይደረጋሉ

You are currently viewing ዛሬ ወደተለያዩ 8 የዓለም ሀገራት በሴቶች ብቻ የሚመሩ በረራዎች በተመሳሳይ ሰዓት ይደረጋሉ

AMN – የካቲት 28/2018 ዓ.ም.

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ዓለም አቀፉን የሴቶች ቀን (ማርች 😎 ምክንያት በማድረግ በስምንት የተለያዩ ሀገራት በሴቶች ብቻ የሚመሩ በረራዎችን እንደሚያደርግ የኢትዮጵያ አየር መንገድ አስታወቀ።

ጉዞውን ለሚያደርጉ ሴት የበረራ ሠራተኞች የሽኝት መርሐ ግብር በተካሔደበት ወቅት የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ ዋና ሥራ አስፈጻሚ መስፍን ጣሰው እንደገለጹት ሴቶች በአቪዬሽን ሙያዎች ውስጥ ያላቸውን ተሳትፎ በጉልህ ማሳየት መቻሉን አንስተዋል።

በኢትዮጵያ አየር መንገድ ውስጥ የሴቶች ተሳትፎ በሁሉም መስክ ማደጉን ያነሱት ዋና ሥራ አስፈጻሚው አሁንም በአየር መንገዱ ከፍተኛ የአመራር ቦታዎችን ጨምሮ በአቪዬሽን ኢንዱስትሪው ውስጥ ሴቶች ትልቅ ሚና እንዲጫወቱ በትኩረት እንደሚሠራ ተናግረዋል።

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ሴቶች ቀደም ሲል በወንዶች ብቻ ተይዘው በነበሩ የሥራ ዘርፎች ጭምር ያላቸውን ገደብ የለሽ አቅም ለዓለም የሚያሳይ መሆኑን የተናገሩት የኢፌዴሪ የሴቶችና ማኅበራዊ ጉዳይ ሚንስትር ኤርጎጌ ተስፋዬ (ዶ/ር) ይህም በመላው ዓለም ያሉ የሴቶችን የጋራ ጥንካሬና ጽናት ዕውቅና የሚሰጥ ነው ብለዋል።

የአየር መንገዱ ተግባር በሌሎችም የመንግስትና የግል የሥራ ተቋማት ሊተገበር የሚገባው አርዓያነት ያለው ተግባር መሆኑን ያነሱት ሚንስትሯ ይህ በጉዟችን ላይ ያስመዘገብነው የዕኩልነት ዕድገትን የሚያሳይ ቢሆንም አሁንም ገና ብዙ ሥራዎች የሚጠይቁን በመሆኑ ሁሉም ባለድርሻ አካል በትኩረት ሊሠራ እንደሚገባው አሳስበዋል።

በመድረኩም የተለያዩ ከፍተኛ የመንግስት የሥራ ኃላፊዎች፣ የተባበሩት መንግታት ድርጅት ተወካዮች እና የተቋሙ ሠራተኞች ተገኝተዋል።

በራሔል አበበ

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review