AMN የካቲት 29/2018 ዓ.ም
የራስን በራስ በመመዝገብ ሂደት ቋሚ የመራጭነት ቁጥር በማግኘት ብቻ ምዝገባዉ እንደማይጠናቀቅ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ አስታወቀ፡፡
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ የራስን በራስ ምዝገባ አስመልክቶ ባወጣዉ ማስታወቂያ የራስን በራስ በመመዝገብ ሂደት ቋሚ የመራጭነት ቁጥር አገኙ ማለት ምዝገባውን አጠናቀዋል ማለት አይደለም ሲል አስታዉቋል፡፡
ቀጣዩን የምዝገባ ሂደት አጠናቀው የ7ኛው ጠቅላላ ምርጫ የመራጭነት ካርድዎን ያግኙ ሲል ቦርዱ በማህበራዊ ትስስር ገጹ ባጋራዉ መረጃ አስታዉቋል፡፡