AMN የካቲት 29/2018 ዓ.ም
በአዲስ አበባ ከተማ እየተከናወኑ የሚገኙ የተለያዩ የልማት ሥራዎች የሴቶችን ፍትሃዊ ተጠቃሚነትን ማዕከል ያደረጉ ናቸው፡፡
የከተማ አስተዳደሩ የሴቶችን ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚነትን ለማሳደግ የብድር አገልግሎት ፣ የገቢ ማሰገኛ ዘርፎች እና የተለያዩ የስራ እድሎችን በመፍጠር ላይ ይገኛል፡፡
የመዲናዋ ሴቶች በሰላምና ግጭት አፈታት እንዲሁም በበጎ ፈቃድ አገልግሎት ላይ ግንባር ቀድም ተሳታፊዎች ሆነዋል፡፡
መስተዳደሩ የለነገዋ የሴቶች ተሃድሶና የክህሎት ማበልጽጊያ ማዕከልን በመገንባትና አስፈላጊውን ድጋፍ በማድረግ ለማህበራዊ ችግር ተጋላጭ የነበሩ ሴቶችን በማሰልጠንና ወደ ስራ በማስገባት ረገድ አርአያነት ያለዉ ተግባራትን በማከናወን ላይ ይገኛል፡፡
ማዕከሉ ከተመሰረተበት ጊዜ አንስቶ በተለያዩ ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ተግዳሮቶች ውስጥ ሆነው ተስፋ ለቆረጡ እህቶቻችን አዲስ የህይወት ምዕራፍ መክፈቻ ሆኗል።
ከንቲባ አዳነች አቤቤ ማዕከሉ ትላንት በጎዳና፣ በችግር እና በተለያዩ ማህበራዊ ቀውሶች ውስጥ የነበሩ ሴቶች ዛሬ ራሳቸውን ችለው ለተሻለ ህይወት እንዲበቁ እያስቻለ ያለ እውነተኛ የተስፋ ማዕከል መሆኑን ገልጸዋል፡፡
ማዕከሉ እስከዛሬ በድምሩ 2 ሺህ 401 ሰልጣኞችን አስመርቆ ወደ ስራ እንዲገቡ በማድረግ ህይወታቸውን በተሻለ መንገድ እንዲመሩና ለሌሎችም ምሳሌ እንዲሆኑ አስችሏል።
በመዲናዋ ሴቶች በውሳኔ ሰጪነትና በኢኮኖሚ ዘርፍ በተለይም በስራ እድል ያላቸው ተሳትፎ እያደገ መምጣቱንም ከንቲባ አዳነች አቤቤ የበጀት ዓመቱን ስድስት ወራት አፈጻጸም አስመልክቶ ለከተማው ምክር ቤት ባቀረቡት ሪፖርት ጠቅሰዋል፡፡
በወንድማገኝ አሰፋ