ሴቶች በድምጻችን በሀገራችን እኩልነትን እናሰፍናለን፣ ብልጽግናን እናረጋግጣለን – ከንቲባ አዳነች አቤቤ

You are currently viewing ሴቶች በድምጻችን በሀገራችን እኩልነትን እናሰፍናለን፣ ብልጽግናን እናረጋግጣለን – ከንቲባ አዳነች አቤቤ

AMN – የካቲት 29/2018 ዓ.ም

ሴቶች በድምጻችን በሀገራችን እኩልነትን እናሰፍናለን፣ ብልጽግናን እናረጋግጣለን ብለዋል ከንቲባ አዳነች አቤቤ፡፡

ከንቲባዋ ይህን የተናገሩት 50ኛውን ዓመት ዓለም አቀፍ የሴቶች ቀን ምክንያት በማድረግ የተዘጋጀው የ5 ኪሎ ሜትር የሴቶች የጎዳና ላይ ሩጫን ባስጀመሩበት ወቅት ነው፡፡

ከንቲባዋ በንግግራቸው ሴቶች ብልጽግናን ማረጋገጥ ብቻ ሳይሆን፣ በእኩልነት እና በብልጽግና ውስጥ እውነተኛ እና ፍትሐዊ የሴቶችን ተጠቃሚነት ዕውን እናደርጋለን ብለዋል።

በተለይም በአትሌቲክሱ ዘርፍ ኢትዮጵያን በዓለም መድረክ ላይ ከፍ አድርገው፣ ሀገራችን አንገቷን ቀና አድርጋ እንድትታወቅ ብሎም ሰንደቅ ዓላማዋ ከፍ ብሎ እንዲውለበለብ ያደረጉት ጀግኖች አትሌቶቻችን በብዛት የተገኙት ከሴትነት መሆኑንም አንስተዋል።

ከንቲባ አዳነች ሴቶች ለሀገራቸው እኩልነት እና ብልጽግና የከፈሉት ዋጋና ያደረጉት ተጋድሎ ገና አልተዘከረም፣ ገና አልተነገረም፣ ደግሞ ካደረግነው በላይ ገና እንሰራለን ነው ያሉት።

ሀገራችንን እናበለጽጋለን፣ እኩልነት እና ፍትሕ እንዲሰፍን እንታገላለን ያሉት ከንቲባዋ በአንድነት እጅ ለእጅ ተያይዘን ከወንድሞቻችን ጋር እንሠራለን ብለዋል።

በወርቅነህ አቢዮ

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review