በኢትዮጵያ የመጀመሪያው በአፍ-ሶማሌ የልጆች መጽሔት ተመረቀ

You are currently viewing በኢትዮጵያ የመጀመሪያው በአፍ-ሶማሌ የልጆች መጽሔት ተመረቀ

AMN-የካቲት 29/2018 ዓ.ም

በኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት የተዘጋጀው እና በኢትዮጵያ የመጀመሪያ የሆነው በአፍ-ሶማሌ “ኡበድሰን” የልጆች መጽሔት በዛሬው ዕለት በጂግጂጋ ከተማ ተመርቋል።

ኡበድሰን በአፍ ሱማሌ “መልካም ልጅ” ማለት ሲሆን፤ ልጆችን የሚያስተምሩ ተረቶች፣ አጫጭር ታሪኮች እና ለትምህርት አጋዥ የሆኑ ይዘቶችንም ያካተተ ነው።

“ኡበድሰን” ከሶስት ዓመት ጀምሮ ያሉ ልጆች እንዲያነቡት የተዘጋጀ መጽሔት ነው።

በምረቃት መርሃግብሩ ላይ የሶማሌ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ሙስጠፌ መሐመድ፣ የክልሉ ትምህርት ቢሮ ኃላፊ አቶ መሐመድ ሼህ አደም፣ የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ መሳፍንት ተፈራ፣ የክልሉ የተለያዩ ቢሮ ኃላፊዎች፣ የሀገር ሽማግሌዎችና የኃይማኖት አባቶች እንዲሁም ሌሎች ባለድርሻ አካላት ተገኝተዋል።

የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት ከዚህ በፊት በአማርኛ “ብላቴናት” በአፋን-ኦሮሞ “ዳኢመን” የተሰኙ የልጆች መጽሔት በየወሩ የሚያሳትም ሲሆን፤ ከአሁን ጀምሮ “ኡበድሰን” መጽሔትን በማካተት በየወሩ የሕጻናት መጽሔቶችን የሚያሳትም ይሆናል።

ዓላማውም፣ ህጻናት የራሳቸውን ባህል፣ ወግ እና እሴት ይዘው እንዲያድጉ እና አንባቢ ትውልድ እንዲፈጠር ነው።

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review