በኢትዮጵያ የአመራር ታሪክ ውስጥ አዲስ ምዕራፍ የከፈቱ ሦስቱ ሴት አመራሮች

You are currently viewing በኢትዮጵያ የአመራር ታሪክ ውስጥ አዲስ ምዕራፍ የከፈቱ ሦስቱ ሴት አመራሮች

AMN- የካቲት 29/2018 ዓ.ም

ሃገራዊ ለውጡን ተከትሎ ሴቶች በማህበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊ እና በፖለቲካዊ ጉዳዮች ላይ በየደረጃዉ እያደረጉት ያለዉ ተሳትፎ ከጊዜ ወደ ጊዜ እያደገ መጥቷል፡፡

በፖለቲካው ዘርፍ በርካታ ሴቶች በኢትዮጵያ ታሪክ የመጀመሪያ በሆኑ የአመራር ቦታዎች ላይ ተቀምጠዋል፡፡

በግንባር ቀደምትነት የቀድሞ ፕሬዝዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ፣ ከንቲባ አዳነች አቤቤ እንዲሁም ኢንጂነር አይሻ መሐመድ ይጠቀሳሉ፡፡

የቀድሞ ፕሬዝዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ የመጀመሪያዋ የኢትዮጵያ ሴት ፕሬዝዳንት በመሆን በሀገር ውስጥ ብቻ ሳይሆን ከዓለም አቀፍ የዲፕሎማሲ መድረክ ትልቅቅ ስራዎችን ሰርተዋል።

ፕሬዝዳንቷ ቀደም ሲል በተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የአፍሪካ ኅብረት ልዩ ተወካይ በመሆን ያገለገሉ ሲሆን፣ በአፍሪካ የሰላም ግንባታ እና የሴቶችን በፖለቲካ የመሳተፍ መብት በማስከበር ረገድ ግንባር ቀደም ተሟጋች ናቸው።

የዓለም የዲፕሎማሲ ማዕከል የሆነችው የአዲስ አበባ የመጀመሪያዋ ሴት ከንቲባ በመሆን በማገልገል ላይ የሚገኙት ከንቲባ አዳነች አቤቤ ሴቶች ከፍተኛ የአመራር ጥበብ እንዳላቸው በተግባር እያሳዩ የሚገኙ ሌላኛዋ የኢትዮጵያ ሴት አመራር ናቸው።

ከንቲባ አዳነች አቤቤ እ.ኤ.አ. በ2024 መቀመጫዉን በእንግሊዝ ያደረገዉ እና በየዓመቱ በአፍሪካ ምርጥ ብቃት ያሳዩ አፍሪካዉያን መሪዎችን የሚሸልመው የአፍሪካ ሊደርሺፕ መጽሄት የሚያዘጋጀው የአፍሪካ የዓመቱ ምርጥ መሪ (African leadership Magazine Person of The Year Award) ሽልማት አሸናፊ ሆነዋል።

እንዲሁም የሃገርን ደኅንነት እና ሉዓላዊነት ለማስከበር በኢትዮጵያ ታሪክ የመጀመሪያዋ ሴት የመከላከያ ሚኒስትር የሆኑት ኢንጂነር አይሻ መሐመድ ሴቶች የሃገር ደኅንነት እና የመከላከያ ውሳኔ ሰጪነት ላይ ያላቸው ሚና አይተኬ መሆኑን አረጋግጠዋል።

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደርም ጠንካራና የበለፀገች ኢትዮጵያን ለመገንባት ብሎም ለትውልድ ለማስተላለፍ እየሰራ ሲሆን 48 በመቶ የአዲስ አበባ ምክር ቤት አባላትም በሴቶች የተያዘ ነው።

በትዝታ መንግስቱ

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review