AMN የካቲት 29/2018 ዓ.ም
ድሬ መሶብ የአንድ ማዕከል አገልግሎት በዉስጡ ምን አካቷል? ምን አይነት አገልግሎቶችን እየሰጠ ነዉ?
የአንድ ማዕከሉ ከ3 ሺ በላይ በሆነ ካሬ ሜትር መሬት ላይ ያረፈ ነዉ
ባለአምስት ወለል ህንጻ እና ቴራስ ያካተተ ነው
ለሥራ ቅልጥፍና አስፈላጊ የሆኑ መሠረተ ልማቶች ተሟልተዉለታል
በውስጡ እንግዳ መቀበያ፣ የህፃናት ማቆያ፣ የጥሪ ማዕከል
የአስተዳደር ቢሮዎች፣ የማሠልጠኛ ክፍሎች ፣ የመረጃና ቴክኖሎጅ ማዕከል
የሁኔታዎች መከታተያ ክፍል፣ የስብሰባ አዳራሽ፤ የመኪና ማቆሚያ እና የካፍቴሪያ አገልግሎት መስጫ ሥፍራዎችን አካቷል።
ማዕከሉ ስራ ከጀመረ ስድስት ወራት ሆኖታል
ማዕከሉ ስራ ከጀመረበት ስድስት ወራቶች ውስጥ በአጠቃላይ ከ23 ሺ በላይ ተገልጋዮችን አስተናግዷል
በውስጡ 10 ተቋማት ይዞ 73 የሚሆኑ አገልግሎቶችን ለዜጎች በመስጠት ላይ ይገኛል
የአንድ ማዕከሉ ተገልጋዮችን የሚያስተናግዱ 96 ካውንተሮች እንዲኖሩት ተደርጎ የተደራጀ ነው።
የተጀመረውን የተቀላጠፈ የዲጅታል አገልግሎት ይበልጥ ለማስፋት አቅዶም እየሠራ ነው