የናሚቢያ ፕሬዚዳንት ሙሉ በሙሉ በሴቶች ለተመራዉ የኢትዮጵያ አየር መንገድ በረራ ደማቅ አቀባበል አደረጉ

You are currently viewing የናሚቢያ ፕሬዚዳንት ሙሉ በሙሉ በሴቶች ለተመራዉ የኢትዮጵያ አየር መንገድ በረራ ደማቅ አቀባበል አደረጉ

AMN የካቲት 29/2018 ዓ.ም

የናሚቢያ ፕሬዚዳንት ኔቱምቦ ናንዲ-ንዳይትዋህ (ዶ/ር) ሙሉ በሙሉ በሴቶች ለተመራዉ የኢትዮጵያ አየር መንገድ በረራ ደማቅ አቀባበል አድርገዋል፡፡

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ዓለም አቀፍ የሴቶች ቀንን በማስመልከት ሙሉ በሙሉ በሴቶች የሚመራ በረራ በማድረግ ላይ ይገኛል፡፡

አየር መንገዱ በሌላ በረራ በካፒቴን አምሳሌ ጓሉ መሪነት ሙሉ በሙሉ በሴቶች የተከናወነ በረራ ወደ ካይሮ ማድረጉን በማህበራዊ ትስስር ገጹ አስታዉቋል፡፡

በረራው የሴቶችን የአመራር ብቃት ፣ ቁርጠኝነት እና በኢንደስትሪው ውስጥ ያላቸውን ሚና ያሳየ መሆኑ እና ግብፅ ካይሮ ሲደርስ ሞቅ ያለ አቀባበል መደረጉንም ጨምሮ ገልጿል፡፡

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review