ማንችስተር ሲቲ ከሊቨርፑል በኤፍ ኤ ካፕ ሩብ ፍፃሜ ይጫወታሉ

You are currently viewing ማንችስተር ሲቲ ከሊቨርፑል በኤፍ ኤ ካፕ ሩብ ፍፃሜ ይጫወታሉ

AMN – የካቲት 30/2018 ዓ.ም

የእንግሊዝ ኤፍ ኤ ካፕ የሩብ ፍፃሜ ዕጣ ድልድል ከደቂቃዎች በፊት ይፋ ሆኗል።

በድልድሉ መሰረት ማንችስተር ሲቲ ከ ሊቨርፑል የሚያደርጉት ፍልሚያ ከወዲሁ ትልቅ ቦታ ተሰጥቶታል።

የፕሪምየር ሊጉ መሪ አርሰናል ወደ ሴንት ሜሪ ስታዲየም አቅንቶ ሳውዛምፕተንን ይገጥማል።

ቼልሲ የሊግ 1 ተወዳዳሪው ፖርት ቬልን በሜዳው ስታምፎርድ ብሪጅ የሚያስተናግድበት ጨዋታም ይጠበቃል።

የዌስትሃም ዩናይት እና ብሬንትፎርድ አሸናፊ ከ ሊድስ ዩናይትድ የሚያደርጉት ጨዋታ ሌላው የሩብ ፍፃሜ ግጥሚያ ነው።

በሸዋንግዛው ግርማ

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review