” ያላገባ ማስረጃ ” ለመስጠት 3ሺህ ብር ጉቦ የተቀበለ ተጠርጣሪ በቁጥጥር ስር ዋለ

You are currently viewing ” ያላገባ ማስረጃ ” ለመስጠት 3ሺህ ብር ጉቦ የተቀበለ ተጠርጣሪ በቁጥጥር ስር ዋለ

AMN የካቲት 30 ቀን 2018 ዓ/ም

በኮልፌ ቀራንዮ ክ/ከተማ አስተዳደር የወረዳ 3 የወሳኝ ኩነት ባለሙያ የሆነው ተጠርጣሪ ተሬሳ አዱኛ የግል ተበዳይ ሀይደር ሬድዋንን ከወረዳው ወሳኝ ኩነት ፅ/ቤት “ያላገባ ማስረጃ” ለመስጠት ለ15 ቀናት ያህል ሲያመላልሰው ቆይቶ በመጨረሻም ማስረጃውን ለማግኘት 3ሺህ ብር ጉቦ መክፈል እንዳለበት ይነግረዋል፡፡

የግል ተበዳይም ገንዘቡን ክፈል መባሉን ለኮልፌ ቀራንዮ ክ/ከተማ ፖሊስ መምሪያ በማሳወቅና የክትትል ቡድን አባላትን በመያዝ ኮልፌ ቀራንዮ ክ/ከተማ ወረዳ 3 ወሳኝ ኩነት ፅ/ቤት በር ላይ ተከሳሽ ገንዘቡን ሲቀበል እጅ ከፍንጅ የተያዘ መሆኑን የክ/ከተማው ፖሊስ መምሪያ አስታውቋል፡፡

ፖሊስ በተጠርጣሪው ላይ ተገቢውን የሰውና የሰነድ ማስረጃ በማሰባሰብና የወንጀል ምርመራ መዝገቡን በማጠናቀር ክስ እንደሚያስመሰርትም ገልጿል፡፡

በመንግስት የስራ ኃላፊነት ቦታ ላይ የሚገኙ አመራሮችም ሆኑ ፈፃሚዎች በህጋዊ አሰራር ያልተገባን ጥቅም ለማግኘት የሚደረግ እንቅስቃሴ ከህግ ተጠያቂነት የማያድን መሆኑን ተገንዝበው ህጋዊ አሰራርን መከተል እንደሚጠበቅባቸው የአዲስ አበባ ፖሊስ ጠቅላይ መምሪያ ለኤኤምኤን በላከዉ መረጃ አስታዉቋል።

ህብረተሰቡም አገልግሎት ለማግኘት በሚሄድባቸው የመንግስት ቢሮዎች የሚያጋጥሙትን መሰል ችግሮች በእጅ ስልኮች የዜጎች ተሳትፎ መተግበሪያን (Citizen Engagement Application) EFPApp በመጠቀም ጥቆማ በመስጠት እንዲተባበር መልዕክቱን አስተላልፏል፡፡

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review