የሀገርን ብልጽግና ለማረጋገጥ እና ዘላቂ ሠላምን ለማጽናት የሃይማኖት ተቋማት አብሮነትና ትብብር የላቀ ሚና ይጫወታል

You are currently viewing የሀገርን ብልጽግና ለማረጋገጥ እና ዘላቂ ሠላምን ለማጽናት የሃይማኖት ተቋማት አብሮነትና ትብብር የላቀ ሚና ይጫወታል

AMN- መጋቢት 1/2018 ዓ.ም

በአራዳ ክፍለ ከተማ ሠላምና ጸጥታ አስተዳደር ጽ/ቤት የመደመር መንግስት ለሃይማኖት ተቋማት ያለው ዕይታ፣ አስተዳደራዊ መርሆዎች፣ ያጋጠሙ ፈተናዎች እና የመፍትሄ አቅጣጫዎችን በሚመለከት ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ የዕምነት አባቶች ጋር የውይይት መድረክ ተካሂዷል።

መንግስት ባለፉት ዓመታት በተለይም የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተ-ክርስቲያንን አንድነት ለማስጠበቅ እና ቅርሶቿን ለመንከባከብ በርካታ ተግባራት ሲያከናውን መቆየቱን የጠቀሱት የውይይቱ ተሳታፊ የዕምነት አባቶች ነገር ግን አንዳንድ የቤተ-ክርስቲያንን ክብር የሚያንቋሽሹ እና ሠላምን ለማደፍረስ የሚሠሩ ማህበራዊ ሚዲያዎችንና የመንገድ ላይ ሰብከቶችን ማስተካከል ይገባዋል ብለዋል።

የዕምነት ተቋማት የሀገርን ሠላም በማጽናት በኩል ትልቅ ሚና እንዳላቸው የተናገሩት በምክትል ከንቲባ ማዕረግ የአዲስ አበባ ከተማ የፋይናንስ ቢሮ ኃላፊ አቶ አብዱልቃድር ሬድዋን፣ እንደ ሀገር የተጀመረውንም የብልጽግና ግንባታ ለማላቅ አስታዋጾኦ ሊያበረክቱ ይገባል ብለዋል።

የዕምነት ተቋማት ትውልድን በማነጽ በሀገር ግንባታ ድርሻ ውስጥ ትልቅ አስታዋጽኦ አበርክተዋል ያሉት የአራዳ ክፍለ ከተማ ዋና ሥራ አስፈጻሚ አቶ ወንድሙ ኡመር፣ ይህንንም ተከታዮቻችንን በማስገንዘብ የበለጠ ልናዳብረው ይገባል ብለዋል።

መንግስት ሁሉንም የዕምነት ተቋማት በዕኩልነት እና በመደመር እሳቤ ይመለከታል ያሉት አቶ አብዱርቃድር ሬድዋን፣ የቤተ ዕምነቶችን ክብርና ከፍታ የሚጎዱ ተግባራትን ለማስስተካከል መንግስት አበክሮ ይሠራል ብለዋል።

ከሠላም ጋር ተያይዞ የሚሠሩ ጉዳዮችንም በጋራ ልንሠራና የዕምነት ተቋማትም በፖለቲካ ለከሠሩት ግለሰቦች መሸሸጊያ እንዳይሆኑ ልንሰራ ይገባል ብለዋል።

ይህንንም ለማስተካከል የዕምነት ተቋማት ከራሳቸው መጀመር እንዳለባቸውና መንግስትም የህግ የበላይነትን ለማረጋገጥና ዘላቂ ሠላም እንዲጸና አስፈላጊውን ሥራ እንደሚሰራም ተናግረዋል።

በአለሙ ኢላላ

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review